የእስራኤል የፖሊስ አዛዥ አስተያየት | ዓለም | DW | 01.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የእስራኤል የፖሊስ አዛዥ አስተያየት

የእስራኤል ከፍተኛ የፖሊስ መኮንን የኢትዮጵያ እና የአረብ የዘር ግንድ ያላቸውን ዜጎችን ከሌሎች ይልቅ የበለጠ በወንጀል ይሳተፋሉ ብሎ መጠርጠር የተለመደ ነው ሲሉ የሰጡት አስተያየት በቤተ-እስራኤላውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:16

የእስራኤል የፖሊስ አዛዥ አስተያየት

የእስራኤል የፖሊስ አዛዥ ሮኒ አልሼይሽ የአገሪቱ ጠበቆች ማህበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ላይ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ «በዓለም ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ወጣቶች እና ስደተኞች አለመመጠን በወንጀል ይሳተፋሉ» ብለዋል። የፖሊስ አዛዡ አስተያየት በቤተ-እስራኤላውያን እና በፖለቲከኞች ከፍተኛ ወቀሳ ቀስቅሶባቸዋል። ከስምንት ሚሊዮን ዜጎች 135,000 ቤተ-እስራኤላውያን ሲሆኑ 17 በመቶው ደግሞ የአረብ ዝርያ ያላቸው ናቸው። የፖሊስ አዛዡ በቤተ-እስራኤላውያን ጉዳይ ያልተመጣጠነ ኃይል ጥቅም ላይ መዋሉንም ተናግረዋል። ለወራት ጠንካራ የአደባባይ ተቃውሞ ያደረጉት ቤተ-እስራኤላውያን አሁንም የፖሊስ አዛዡ ከሥራቸው እንዲባረሩ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ከእነዚህ መካከል ሶሻል ወርከር የሆኑት ወ/ሮ አማረች አለፈ ይገኙበታል።

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic