የእስራኤል የጋዛ ድብደባ መቆም | ዓለም | DW | 05.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የእስራኤል የጋዛ ድብደባ መቆም

የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ከመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሰው ነበር ። ላለፉት 28 ቀናት በተካሄደው ድብደባ ቤታቸው ታስረው የቆዩት ፍልስጤማውያንም ዛሬ መንገዶችንና ገበያዎችን ሞልተው ታይተዋል ።

እስራኤል በጋዛ ለ4 ሳምንታት ያካሄደችውን ድብደባ ዛሬ ጋብ አድርጋ የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም አውጃለች ። የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች ዛሬ ጋዛን ለቀው እስራኤል ድንበር ላይ ሰፍረዋል። ሆኖም የእስራኤል ጦር ለሚሰነዘርበት ማናቸውም ጥቃት የአፀፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ። የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ከመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሰው ነበር ። ላለፉት 28 ቀናት በተካሄደው ድብደባ ቤታቸው ታስረው የቆዩት ፍልስጤማውያንም ዛሬ መንገዶችንና ገበያዎችን ሞልተው ታይተዋል ። ዛሬ ተግባራዊ ስለሆነው የተኩስ አቁምና ተግባራዊነቱ እንዲሁም ስለ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሃይፋውን ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ግርማው አሻግሬ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic