የእስራኤል የመንግሥታቱ ድርጅት ዉሳኔ ተቃዉሞ  | ዓለም | DW | 27.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የእስራኤል የመንግሥታቱ ድርጅት ዉሳኔ ተቃዉሞ 

እስራኤል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ውሳኔ በኋላ ከ12 ሃገራት ጋር ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። ግንኙነቱን ያቋረጠችው ምዕራብ ዮርዳኖስ እና ምሥራቅ ኢየሩሳሌም የአይሁድ ሰፈራን በማውገዝ የመንግሥታቱ ድርጅት ዐርብ እለት ያሳለፈውን ውሳኔ  በመቃወም ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:34
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:34 ደቂቃ

እስራኤል ከ12 ሃገራት ጋር ሥራ አቋረጠች

እስራኤል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ውሳኔ በኋላ ከ12 ሃገራት ጋር ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። እስራኤል ከሃገራቱ ጋር የሥራ ግንኙነቱን ያቋረጠችው በምዕራብ ዮርዳኖስ እና ምሥራቅ ኢየሩሳሌም የአይሁድ ሰፈራን በማውገዝ የመንግሥታቱ ድርጅት ዐርብ እለት ያሳለፈውን ውሳኔ  በመቃወም ነው። ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብሎ የእየሩሳሌም ወኪላችን ዜናነህ መኮንንን በስልክ አነጋግሬው ነበር። ዜናነህ ውሳኔው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንሥትር የዓመታት ውዝግብ ውጤት ነዉ ብሏል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ/ ዜናነህ መኮንን
አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic