የእስራኤል ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉብኝት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2001ማስታወቂያ
ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር ሊበርማን በዚህ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ ኡጋንዳ ናይጀሪያ እና ጋናም ይሄዳሉ ። ከርሳቸው ጋርም ሀያ የእስራኤል ነጋዴዎችና የኩባንያዎች ባለቤቶች አብረው ተጉዘዋል ። አንድ የእስራኤል ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር ከሀያ ዓመት ወዲህ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሀገራት ጉብኝት ሲያደርግ ሊበርማን የመጀመሪያው ናቸው ። የሊበርማን የኢትዮጵያ እና የሌሎች አራት የአፍሪቃ አገራት ጉብኝት ዓላማ ላይ በማተኮር የእየሩሳሌሙ ወኪላችን ዜናነህ መኮንን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ዜናነህ መኮንን ፣ሂሩት መለሰ