የእስራኤል እና የፍሊስጤም ግጭት | ዓለም | DW | 19.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የእስራኤል እና የፍሊስጤም ግጭት

የእስራኤልና የፍሊስጤም ሚሊሻዎች በሮኬትና በቦምብ ጥቃት ከጀመሩ ዛሬ ስድስተኛው ቀን ነው። የእስራኤል ጥቃት ከጀመረበት ካሳለፍነው ረቡዕ ወዲህ ትናንት ለጋዛ እጅግ አሳዛኝ ቀን ነበር። በጋዛ ከተማ ቤቶች ላይ ያነጣጠረ የእስራኤል የአየር ጥቃት ቢያንስ 11 ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድል 30 የሚሆኑትን አቅስሏል።

የእስራኤል ጥቃት ከጀመረ ወዲህ ዘጠና ፍሊስጤማዊያን ሲገደሉ፣ ከነኚህም ውስጥ 21 ህጻናትና በርካታዎቹ ደግሞ ሴቶች ናቸው። ከጋዛ የተወነጨፉ ሚሳዬሎችም ሶስት የእስራኤል ወታደሮች ሲገድል በርከት የሚሉትን አቁስሏል። እስራኤል በባህር ኃይሏ የዘጋችውን የጋዛ ሰርጥ ግዛት መልሳ እንድትከፍትና በአዛዦቹ ላይ የሚካሄደውን የተቀነባበረ ግድያ እንድታቆም ሐማስ ጠይቋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በተቃራኒው በታንክና እግረኛ ጦር የታገዘ ወረራን ጋዛ ላይ ለማስከድ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። መጽሔታችን በአዲሱ የእስራኤልና ጋዛ ውጥግብ ላይ ያተኩራል።

እአአ አቆጣጠር በ1993 የያነው የፍሊስጤም መሪ ያስን አራፋትና የእስራኤል አቻቸው ይሻቅ ራቢን የኦስሎን ስምምነት ከፈረሙ ወዲህም እንኳ እስራኤል ደጋግማ የፍሊስጤምን ግዛቶች ይዛለች። ምክንያቷም ወረራው፣ ለእስራኤል፣ እንዲው ግዛትን መቆጣጠር ሳይሆን የራስን ህልውና የመከላከል መብት ነው። እስራኤል ታዲያ በዚህ የምድር ጥቃት ዬትኛውን ዓላማ ከግብ ማድረስ ትችላለች? እስራኤልን የሚተቹ ወገኖች እንደሚሉት ጥቃቱ እስራኤል ሆን ብላ ግጭቱን ለማካራር የምታደርገው ጥረት ነው። ከመጋረጃው በስተጀርባ ከእስራኤል ጋር በተኩስ አቁም ጉዳይ ላይ ይደራደሩ የነበሩ የሐማስ የጦር መሪ አህመድ አል ጃባሪ በእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች ባሳለፍነው ረቡዕ ተገድለዋል።

ዮሔን ሂፕሌር በጀርመን ዲዩስበርግ ኤሰን ዩኒቨርስቲ የልማትና ሰላም ተቋም ተመራማሪ ሲሆኑ የእስራኤል የሀገር ውስጥ ፖሊቲካ አዲስ ሊካሄድ በታቀደው ወታደራዊ ጥቃት ውስጥ ልዩ ሚና ይጫወታል ይላሉ።

epa03477616 German Foreign Minister Guido Westerwelle speaks to reporters as her arrives at a European Foreign affiars ministers meeting in Brussels, Belgium 19 November 2012. Reports state that the meeting will mainly focus on the conflict between Israel and Palestine and evolution of the situation in Syria. EPA/OLIVIER HOSLET

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ ፍልስጤማውያን ወደ እስራኤል ከተሞች ሮኬት መተኮስ እንዲያቆሙ አሳስበዋል

«የእስራኤል መንግስት አሁን በምርጫው ዘመቻ ምክንያት ግጭቱን ለማባባስ ሆን ብሎ እየሰራ ያለ ይመስላል። ይህ የእግረኛ ጦር ዘመቻ የተፈለገውን ውጤት ላያመጣ ይችል ይሆናል።»
እአአ በጥር 22፣ 2013 በእስራኤል አዲስ ፓርላማ ይመረጣል። የእስራኤል ህዝብ በርግጥም የጸጥታ ጉዳይ ስለሚያሳስበው ጠንከር ያሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ይፈልጋል። ሆኖም ግን እንደ ጆሄን ሂፕለር እምነት የእስራኤል ወታደሮች እየተገደሉ ረዥም ጊዜ የሚወስድ የምድር ጥቃት ቢካሄድ የእስራኤል መንግስት የህዝብን ድጋፍ ያጣል።

ሳይንስና ፖሊቲካ በተሰኘው የጀርመን ተቋም ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ የፖሊቲካ ባለሙያው ጊዲ ሽታይንበርግ በእስራኤልና ሐማስ መካከል እየተካሄደ የነበረው ድርድር አደጋ ላይ ነው ይላሉ፣ «እንደሚመስለኝ በጣም ጎልቶ የሚታየው ምክንያት በ2012 ከሐማስ በኩል የሮኬት ጥቃት እየባሰበት መሄዱ ነው። በርግጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግና ለመደራደር ጥረቱ ነበረ። በስተመጨረሻ ግን እስራኤል የሐማሱን የጦር መሪ ስትገድል ጥረቱ ተሳናክሏል።»

ሐማስን በአየር ኃይል ጥቃት የማዳከም ጥረት ብዙም የሚሳካ አይደለም። በጋዛ ኮረብታዎች የሚገኙ መንደሮች እጅግ ከተጨናነቁ የዓለማችን መንደሮች ውስጥ አንዱ ነው። እስላማዊው ሚሊሻዎችም በከፊል የሚንቀሳሱ በዚሁ መንደር ውስጥ ነው።

ባለፉት ዓመታት እንደታየው እስራኤል የሐማስን የሮኬት ማስወንጨፊያ ይዞታዎችን ብታወድምም፣ ሐማስን ግን ከፖሊቲካ ሜዳው ማስወጣት አልቻለችም። ከአራት ዓመታት በፊት ነበር እስራኤል ጋዛን የወረረች። ሶስት ሳምንት በቆየው «ካስት ሊድ» በተሰኘው ወታደራዊ እርምጃ 1300 ፍሊስጤማዊያንና አስራ አራት እስራኤላውያን ተገድለዋል። ሐማስ ግን አሁንም ከፖሊቲካው ሜዳ አልወጣም። የዱይስበርግ ኤሰን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ጆሄን ሂፕለር የአሁኑ የምድር ጦር ጥቃትም መክሸፉ አይቀርም ይላሉ፣ «የእስራኤል ወታደሮች አንድ ቀን ዘመቻውን ፈጽመው በሚመለሱበት ጊዜ፣ የፍሊስጤም ህዝቦች እስራኤል በምትፈልግ መንገድ አይጓዙም።»

በተቃራኒው የሐማስ ስቃይ የድርጅቱን ህጋዊነት በፍሊስጤማዊያን ልብ ውስጥ እንዲሰርጽ ያደርጋል እንጂ። በሀገር ውስጥ ፖሊቲካ ጠንካራው የሐማስ ተፎካካሪ የሆነው ምዕራብ ዮርዳኖስን የሚያስተዳድር የፋታህ ፓርቲም ቢሆን የፖሊቲካው ውድድር አካል ነው። በጀርመን የሳይንስናና ፖሊቲካ ተቋም ባለሙያ ጊዶ ሽታይንበርግ እንደሚሉት ሀማስን ከጋዛ ማስወገድ ለእስራኤል ተገቢው ውሳኔ አይሆንም፣
«ቀላል የሆነ አማራጭ የለም። በራማላህ የሚገኝ የፍሊስጤም ባለስልጣን ጋዛን የማስተዳደር ኃላፊነት ተቀብሎ የመወጣት አቅም የለውም።» በተጨማሪም አክራሪ የሙስሊም ቡድኖች ለረዥም ጊዜያት የሮኬት ጥቃቶችን ሲያደርሱ ቆይተዋል። እስከ ዛሬም እኒኚን እክራሪ ቡድኖች በሰፊው ተቆጣጥሮ የነበረው ሐማስ ሲሆን፣ እስራኤልንም እንዳያጠቁ በከፊል ሲከላከል ነበር። የአሁኑ ጥቃት ለአክራሪ ቡድኖቹ መጠናከር ምክንያት ሊሆን ይችላል ይላሉ ሂፕለር፤

«ሐማስም ሆነ ፋታህ ፍሊስጤምን ከእስራኤል ጦር እርምጃ መከላከል አይችሉም የሚል ምክንያት ስለሚፈጥራለቸው፣ እነኚ ቡድኖች ምናልባት ከበፊቱ ተጠናክረው ሊመጡ ይችላሉ።» በእስራኤልና የፍሊስጤሙ ሐማስ መካከል የተፋፋመውን ግጭት ለማርገብ የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሂሻም ካንዲል ባለፈው ዓርብ ወደ ጋዛ ሰርጥ ተጉዘዋል። በካይሮ ሥልጣን ላይ ያለው የሙስሊም ወንድማማቾች፣ የሐማስ እህት ድርጅቶች ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው። ከአረቡ የህዝብ አቢዮት መቀስቀስ ወዲህ የግብጽ መንግስት ከህዝብ ያለውን ተቀባይነት ሳያጣ በእስራኤልንና የምዕራብ ፖሊቲካን ጸጥ ብሎ መመልከት አይችልም ይላሉ ጊዶ ሽታይንበርግ። በአዳጊው የግብጽ ዲሞክራሲ ውስጥ መንግስት ለህዝቡ ተጠሪ መሆን ግድ ይለዋል። ጠቅላላ የግብጽ ህዝቡም ሆነ የሙስሊም ወንድምማማቾች እስራኤልን በወቀሳ ዓይን ይመለከታሉ።

«የአረብ አቢዮት ግብጽ ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የእስትራቴጂ ቅድሜ ሁኔታዎችን የቀየረ ብቻ ሳይሆን መጥፎም አድርጎታል።» እአአ በ2009 በተደረገው የጋዛ ጦርነት ሆስኒ ሙባሬክ ለእስራኤል በማድላት ግዛቱን ዘግተው እንደነበር ይታወሳል። አሁን ግን ካይሮ ምን ዓይነት መልስ መስጠት እንደምትችል እስራኤል በያንዳንዱ እርምጃ ማጠን ይኖርባታል። ጆሄን ሂፕለር እንደሚሉት ከሆነ እስራኤል ምናልባት ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደገና መገለል ሊደርስባት ይችላል፣

«የጸጥታው ፖሊቲካ የምድር ጦር ጥቃቱን ትርጉም ያሳጠዋል። እስራኤል ከግብጽ ጋር መጠናከር የሚገባውን ግንኑነቷን የፖሊቲካ ሸክም ልታደርግ ትችላለች። አሁንም የጋዛው ዓላማ ሳይሳካ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መገለል ይመጣል። ቀድሞውኑ እዚያው በጎረቤቷ ሶሪያ ሊፈታ የሚገባ ከበቂ በላይ ችግር አለ።»

ለዚህ የእስራኤልና የፍሊስጤም የፖሊቲካ አታካራ መፍትሔ ሐሳብ ለማፈላለግ የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ዌስተዌሌ ዛሬ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ያቀናሉ። እዚያም የእስራኤልና ፍሊስጤም ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል። ቻይናም በበኩሏ በግጭቱ የሚሳተፉ አካላት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አፈ ጉባኤ ሁዋ ቹንዩንግ በኩል ጥሪ አቅርባለች። በብራሴልስ ስብሰባ ላይ ያሉ የአውሮፓ ህብረት የውጭና የመከላከያ ሚኒስትሮች በጋዛ ሰርጥ እየታየ ያለው የሰው ህይወት መጥፋት አሳስቧቸዋል። አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነትም በእስራኤልና በሐማስ መካከል እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic