የእስራኤል አሰሳና ፍልስጤማውያን
ሰኞ፣ ሰኔ 16 2006ማስታወቂያ
እስራኤል የደረሱበት ባልታወቀው ሶስት እስራኤላውያን ተማሪዎች ፍለጋ ምክንያት በፍልስጤም ምድር የጀመረችውን አሰሳ አሁንም አጠናክራ ቀጥላለች ። ትናንት ለሊት በጀኒን ና በሄብሮን በተካሄደ አሰሳ 37 ተጠርጣሪ ፍልስጤማውያን ታስረዋል ።በዚሁ ዘመቻ የእስራኤል ወታደሮች ቤተልሄምና ናብሉስም መግባታቸው ተገልጿል ። እገታውና በተከታታይ የቀጠለው እስር ሃማስና የፍልስጤማውያን ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ በተፈራረሙት የአንድነት ስምምነት ላይ ተፅእኖ በማድረግ ላይ መሆኑ ተዘግቧል ።ከእገታው በኋላ እስራኤል በአንዳንድ ኬላዎች ጥብቅ ቁጥጥር ማካሄዷና አንዳንዴም መዝጋትዋ እንቅስቃሴዎችን አውኳል ። በእርምጃው የሰዎች ህይወት መጥፋቱን በርካታ ሰዎችም መታሰራቸው እስራኤልን በመብት ጥሰት እያስወቀሳት ነው ። ስለ ቀጠለው የእስራኤል እርምጃ የሃይፋውን ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ