የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የጀርመን ጉብኝት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 28.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የጀርመን ጉብኝት

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ሄታንያሁ ከትናንት በስትያ በጀመሩት የጀርመን ጉብኝታቸዉ ከጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ጋር ተነጋግረዋል።

default

ከመራሂተ መንግስት አንገላ ሜርክል ጋር ተገናኝተዉ የተነጋገሩ ሲሆን የንግግራቸዉ ዋና ርእስ የመካከለኛዉ ምስራቅ የሰላም ሁኔታ፣ የኢራን የኒኩሊየር መረሃ-ግብር እና የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ላይ ያተኮረ ነበር። እስራኤል እና ፍልስጤም በመካከላቸዉ ያለዉን ዉጥረት አርግበዉ ለሰላሙ ጥረት የየበኩላቸዉን አስተዋጾ ካደረጉ ይላሉ የጀርመንዋ መረሂተ መንግስት አንገላ ሜርክል በሁለቱ አገሮች መካከል የተዳፈነዉ የእስራኤል-ፍልስጤም የሰላም ድርድር ዳግም ለመጀመር እድል ይኖረዋል የሚል እምነት አለኝ። የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት እስራኤል በፍልስጤም ክልል የጀመረችዉን የሰፈራ ጣብያ ግንባታ እንድታቆም በጥብቅ ጠይቀዋል። የሰፈራዉ ጉዳይ ከቆመ ይላሉ በሁለቱ መንግስታት መካከል ያለዉን መቃቃር ለመግታት እና በሁለቱ መንግስታት መካከል የተዳፈነዉን የሰላም ድርድር ለማካሄድ የሚረዳ የመጀመርያ ጥርግያ መንገድ ነዉ።
«ከሁሉ በተጨማሪ እዚህ ላይ ጥንቃቄ መወሰድ ያለበት፣ በሰፈራዉ ጣብያ ግንባታ የተነሳ የፍልስጤም ግዛት ምስረታ ጉዳይ መታወክ የለበትም»
መራሂተ መንግስት አንገላ ሜርክል ከፍልስጤሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ሄታንያሁ ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ይህንኑ አቋማቸዉን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ግን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ለተናገሩት ንግግር የሰጡት አወንታዊ መልስ አልነበረም። በሌላ በኩል ኔታንያሁ የሁለቱ አገራት መንግስታት የሰላም ንግግር እንዲያደርጉ መፈለጋቸዉ በድጋሚ አሳዉቀዋል። ለዚህም ፍልስጤም የእስራኤልን ልእልና መቀበልዋ የሰላሙ መፍትሄ ምሶሶ መሆኑ ነዉ የገለጹት
«ከመራሂተ መንግስቷ ጋር ይህንን ዉጥረት እና ብጥብጥ ለማቆም ስላለኝ አቋም ጉዳይ ተነጋግሪያለሁ። ሰላም ለማግኘት ያለን የስሌት መረሃግብርም ከጦር መሳርያ ነጻ የሆነ፣ የይሁዳን መንግስት ልዋላዊነት የሚቀበል የፍልስጤም መንግስትነወምንሻዉ

Flash-Galerie Aussenminister Frank-Walter Steinmeier und der israelische Ministerpraesident Benjamin Netanjahu

የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ሄታንያሁ


እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ሄታንያሁ ገለጻ ለፍልስጤም ህዝቦች ሰላም ለመስጠት እና ህይወትን ቀላል ለማድረግ መንግስታቸዉ ለሰላሙ ጥረት የመጀመርያዉን እርምጃ አሳይቶአል። ይህን ሲሉ እስራኤል በፍልስጤም ክልል የነበራትን የመቆጣተርያ ጣብያ ፣ያጠረችዉን መገናኛ መንገድ አንስታለች፣ እንዲሁም የተቆጣጠረችዉን የንግድ ክልሎች ለቃለች በማለት ኔታንያሁ በድጋሚ ይገልጻሉ
«በአንድ ወይም በሁለት ወራቶች ዉስጥ የሰላሙን ድርድር እንጀምራለን ብዮ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህንኑ የሰላም ድርድር ስልጣን እንዳዝኩ ጀምሪ ማለት የዛሪ አራት ወር ግድም ማድረግ እንችል ነበር። ለሰላም ጥረቱ ሁልግዜም ቢሆን ዝግጁ ነበርኩ አሁንም ዝግጁ ነኝ»
ሜርክል እና ኔታንያሁ እስራኤል ጠንካራ የማስፈራርያ ዛቻ ሆኖ ስለሚሰማት ስለ ኢራኑ የኑክሌር መርሐ-ግብር ተነጋግረዋል። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ስለ ኢራኑ የኒኩሊየር መረሃግብር በበኩላቸዉ ለስምንቱ በኢኮነሚ ለበለጸጉት አገሮች ስብሰባ ላይ የመነጋገርያ ነጥብ ሆኖ እንዲቀርብ አደርጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
«ኢራን የኑክሊየር መረሃ ግብሯን አቁማ ለሰላሙ ጥረታችን አጥጋቢ ዉጤት ካላመጣን ጠንካራ የሆነ አቋም እንወስዳለን። የኸዉም የሃይል ምንጭ ቅነሳን በተመለከተ አልያም ሌላ በጣም አስፈላጊ የሆነን ነገር ማለት እንደ ትልልቅ የንግድ ልዉዉጦችን ማገድ እናስባለን፣ ማሰብ ብቻ ሳይሆን አለማቀፉ ህብረተሰብ ሁኔታዉን አይቶ እገዳዉን በተግባር እንዲፈጽመዉ እንነጋገራለን»
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክር ቤት በኢራን ጉዳይ ማእቀብ ይጣል አይጣል ዉሳኔ ላይ ሳይደርስ ኢራን ላይ ካስፈለገ ጠንካራ ማቀብ መጣል አለበት የእስራኤል ሃሳብ ነዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያሚን ኔታንያሁም በዚህ ጉዳይ ላይ የአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጠንካራ አቋም እንዲይዝ ነዉ ምኞታቸዉ። ከትናንት ወድያ በርሊን የገቡት የእስራኢሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያሚን ናትያሁ ወደ ጀርመን ከመምጣቸዉ ቀደም ሲል በለንደን ከብሪታንያዉ አቻቸዉ ከጎርደን ብራዉንና ጋር በፍልስጤም እና በእስራኤል እንዲሁም በመካከለኛዉ ምሥራቅ ዘላቂ ሰላም በሚመጣበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸዉ ይታወሳል።
አዜብ ታደሰ፣ ሂሩት መለሰ