የእስራኤሉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በአዉሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የእስራኤሉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በአዉሮጳ

ፅንፈኛዉ ፖለቲከኛ የበርሊን ቆይታና ዉይይታቸዉ ከመገናኛ ዘዴዎችና ከፎቶግራፍ-አንሺዎች የተደበቀ ነበር

default

አቪግዶር ሊበርማን

አራት የአዉሮጳ ሐገራትን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት አዲሱ የእስራኤል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን ትናንት በርሊን ዉስጥ ከጀርመን ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግረዋል።ሊበርማን ከበርሊን በፊት ሮምና ፓሪስን ጎብኝተዉ ነበር።ዛሬ ደግሞ ፕራግን ይጎበኛሉ ተብሏል።በየደረሱበት ሕዝባዊ የተቃዉሞ ሠልፍ፥ ዉግዘትና ትችት የገጠማቸዉ ቀኝ ፅንፈኛዉ ፖለቲከኛ የበርሊን ቆይታና ዉይይታቸዉ ከመገናኛ ዘዴዎችና ከፎቶግራፍ-አንሺዎች የተደበቀ ነበር።የሊበርማንን ጉብኝትና የተደበቀበትን ምክንያት ይልማ ሐይለሚካኤል ከዚያዉ ከበርሊን ተከታትሎታል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ