የእስረኞች የሰብዓዊ መብት አያያዝ | ኢትዮጵያ | DW | 16.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የእስረኞች የሰብዓዊ መብት አያያዝ

በኢትዮጵያ ዳግም የታወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈፅመዉ ኮማንድ ፖስት ብዙ ሰዎችን ማሰሩ እየተዘገበ  ይገኛል። የሰብዓዊ መብት ሁኔታን የሚከታተል መርማሪ ቦርድ የታሳሪዎቹን በየእስር ቤቶቹ ተዘዋዉሮ በማየት ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:03

የእስረኞች አያያዝ

መርማሪ ቦርዱ በኦሮሚያ ክልል «በሰሜን ሸዋ ንዑስ ቀጠና 4፣ በአምቦ ንዑስ ቀጠና 34፣ በወሊሶ ንዑስ ቀጠና 14» የሚገኙትን ተጠርጣሪዎች መጎብኘቱን የሃገርቱ የዜና አዉታሮች ሰሞኑን ዘግበዋል።

በዘገባዉ መሰረት መርማሪ ቦርዱ በፊቼ፣ አምቦና ወሊሶ ዉስጥ ተይዘዉ የሚገኙት እስረኞች አያያዝና ምርመራ ሰብአዊ መብትን የጠበቀ ነዉ ቢልም በቂ ምግብና ህክምና እያገኙ አለመሆኑን ለአገር ዉስጥ መገናኛ ብዙኃን አሳዉቀዋል። ዘገባዉ እርስበርሱ እንደምቃረንና ከሕግ ጋር እንደሚፋለስ የሕግ ባለሙያ አቶ ዋንድሙ ኢብሳ ተናግረዋል።

የተጠርጣርዎች ቁጥር መብዛቱና በፌዴራል የተበጀተዉ ባጀት በግዜዉ አለመድረሱ የምግብና የሕክምና አገልግሎት በሚፈለገዉ መጠን መድረስ አለመቻሉ እንደ ምክንያት መጠቀሱን ዘገባዉ አክሎበታል። አቶ ወንድሙ መንግስት ሕገ-መንግስቱን አስከብራለሁ፣ የመንግስት አሰራርን ተጠያቅነት እንዲኖረዉ አድርጋለሁ ከሚለዉ ጋር እንደማይመጣጠን ይናገራሉ።

ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ኮማንድ ፖስቱ እስካሁን ከያዛቸዉን ተጠርጣርዎች ዉስጥ እነዚህ ይከሰሱ፣ እነዚህ ደግሞ ይፈቱ ብሎ እስካሁን አለመወሰኑን ተናግረዋል።

ከአስተያየት ሰጭዎች መካከል ከመጀመሪያው የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊ አለመሆኑ ተነግረዉ ነበር፣ አሁንም እንዲነሳ የሚል ሀሳብ እንዳላቸዉ የፅሁፍ አስተያየታቸዉን ልከዉልናል። በግፍ አስሮ ሚያሰቃያቸውን ወገኖቻችንን በሙሉ ይልቀቅ፣ የተበደሉትን ይካስ በዳዮችን(ገዳዮችን) ለፍርድ ያቅርብ፣ ወጣት አስሮ፣ገሎ፣ለስደት እየዳረጉ ለውጥ እና ልማት ማምጣት አይቻልም ሲሉም አስተያየታቸዉን ልከዉልናል።

ይህ የዜና መፅሄት አየር ላይ እስከምዉል ድረስ ከመርማር ቦርዱ አባላት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic