የእስረኞች መፈታትና የአዉሮጳ ኅብረት ምላሽ  | የጀርመን ምክር ቤታዊ ምርጫ | DW | 09.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

የጀርመን ምክር ቤታዊ ምርጫ

የእስረኞች መፈታትና የአዉሮጳ ኅብረት ምላሽ 

የአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት እስረኞችን በይቅርታ ለመልቀቅ መወሰኑን አዎንታዊ እርምጃ ሲል አወደሰ። በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካ ተሀድሶንም እንደሚደግፍ አስታወቀ። ህብረቱ ከዚሁ ጎን ለጎን የተቃዋሚ ሰልፈኞች ጥያቄዎችም በውይይት እንዲፈታ አሳስበዋል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:16

የአውሮጳ ኅብረት የእስረኞችን በይቅርታ ለመልቀቅ መወሰኑን አዎንታዊ እርምጃ ብሎታል።

 

የአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት እስረኞችን በይቅርታ ለመልቀቅ መወሰኑን አዎንታዊ እርምጃ ሲል አወደሰ። በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካ ተሀድሶንም እንደሚደግፍ አስታወቀ። የህብረቱ ቃል አቀባይ ካትሪን ሬይ ዛሬ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ባለፉት ሳምንታት በሺህዎች የሚቆጠሩ እሥረኞች መፈታታቸው እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዷለም አራጌን ጨምሮ ሌሎችንም ታራሚዎች ለመፍታት መወሰኑ ትክክለኛ አቅጣጫን የሚያሳይ እርምጃ ነው ብለዋል ከዚሁ ጎን ለጎን የተቃዋሚ ሰልፈኞችን ጥያቄዎችም በውይይት እንዲፈታ አሳስበዋል። 


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic