የእስረኛዉ የረሐብ አድማ | ኢትዮጵያ | DW | 02.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የእስረኛዉ የረሐብ አድማ

የአቶ ናትናኤል ፓርቲ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) የቂሊንጦ ወሕኒ ቤት እርምጃን ተቃዉሟል። ከቀድሞዉ የአንድነትና የመድረክ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከአቶ አንዱ አለም አራጌ ጋር በአሸባሪነት የተከሰሱት አቶ ናትናኤል አስራ-ሥምንት ዓመት ተፈርዶባቸዉ ይግባኝ ብለዉ እየተሟገቱ ነዉ

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Dr. Negasso Gidada Thema: Der ehemalige Staatspräsident und heutige Vize-Vorsitzender des Achtparteien-Oppositionsbündnisses „Medrek“ , Dr. Negasso Gidada, ist vor der Wahl ein gefragter Gesprächspartner Schlagwörter: Negasso Gidada, Medrek, Forum, Äthiopien 2010, Äthiopien Opposition, Ethiopia 2010, Wahl Äthiopien

የአንድነት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶበአሸባሪነት ክሥ አስራ-ሥምንት ዓመት እስራት ተበይኖባቸዉ ወሕኒ ቤት የሚገኙት የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ናትናኤል መኮንን የረሐብ አድማ መቱ።አቶ ናትናኤል አድማዉን የመቱን ቤተ ሠብ፥ ዘመድ እና ወዳጅ እንዳይጠይቃቸዉ፥ ምግብና አላቂ ቁሳቁስ እንዳይደርሳቸዉ የታሠሩበት የቂሊንጦ ወሕኒ ቤት ማገዱን በመቃወም ነዉ።የአቶ ናትናኤል ፓርቲ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) የቂሊንጦ ወሕኒ ቤት እርምጃን ተቃዉሟል። ከቀድሞዉ የአንድነትና የመድረክ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከአቶ አንዱ አለም አራጌ ጋር በአሸባሪነት የተከሰሱት አቶ ናትናኤል አስራ-ሥምንት ዓመት ተፈርዶባቸዉ ይግባኝ ብለዉ እየተሟገቱ ነዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic