የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ | ኤኮኖሚ | DW | 16.06.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ

ከሣሃራ በስተደቡብ የሚገኘው የአፍሪቃ ክፍል ዛሬም አያሌ ሕዝብ ከዝቅተኛው የድህነት መስፈርት በታች ኑሮውን የሚገፋበት የዓለም አካባቢ ነው።

default

አብዛኛው ነዋሪ አርሶ አደር ሆኖ ሳለ የእርሻና የገጠሩ ልማት የሚገባውን ያህል እንዲራመድ አልተደረገም። የምግብ ዋስትና በሚገባ ባለመረጋገጡ ጥቂት እንኳ ዝናብ በጠፋ ቁጥር ኢትዮጵያን በመሳሰሉት አገሮች ለረሃብና ለረሃብ ሞት የሚጋለጡት ብዙዎች ናቸው።
ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በአፍሪቃ ታየ የተባለው የኤኮኖሚ ዕድገትም የገጠሩን ልማት መሠረቱ ባለማድረጉ በብዙሃኑ የማሕበራዊ ኑሮ መሻሻል ሊከሰት አልቻለም። ያለፉት ሁለት ዓመታት ዓለምአቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ደግሞ ድህነቱን ይበልጥ ሲያባብስ የኑሮ ውድነትና በተለይም የምግብ ዋጋ መናር ማሕበራዊ ቀውስን እንዳያስከትል ማስጋቱን ዛሬም የቀጠለ ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ ከዚህ አዙሪት መውጣት የሚቻለው እንዴት ነው? የአፍሪቃን የእርሻና የገጠር ልማት እንዴት ለማሻሻል ይቻላል? ያለፉት ሰላሣ ዓመታት የሕዝባዊት ቻይና ልምድስ በአርአያነት ሊወሰድ ይችላል ወይ? በነዚህና ከነዚሁ በተሳሰሩ ጥያቄዎች ላይ ባለፈው ሣምንት በዚህ በቦን ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት ሣይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ባለሙያ ዶር/ዳዊት ተሥፋዬን ማነጋገራችን ይታወሣል። በዚሁ ቃለ-ምልልስ ላይ በማተኩር ዛሬ ደግሞ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ የሚያተኩረውን ሁለተኛና ማጠቃለያ ክፍል እናቀርባለን።

ከሣሃራ በስተደቡብ አፍሪቃ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ ባለፉት ሰላሣ ዓመታት ቻይና ውስጥ የታየውን የዕርሻ ልማት ዕርምጃ እንዳለ መገልበጥ መቻሉ ያጠያይቃል። ግን በዶር/ዳዊት ተሥፋዬ ዕምነት በኢትዮጵያም ለዘርፉ ሰፊ ትኩረት መሰጠቱና ተገቢውን ፖሊሲ ማራመዱ ቅድመ-ግዴታ ይሁን እንጂ የቻይናው ዕርምጃ ቢቀር በረጅም ጊዜ ለደረስበት የሚችል ነው። እርግጥ የአስተራረሱን ዘይቤ፣ የገበያውን ይዞታና የምርት መበራከትን፤ በተለይም ደግሞ ግቡን በተመለከተ የፖሊሲ ለውጦች እንዲራመዱ መደረግ ይኖርበታል። የቃለ ምልልሱን ይዘት ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን