የእሥራኤል ሠፈራና የአውሮፓው ኅብረት፣
ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2005ማስታወቂያ
በ 1959 ዓ ም ፤ በእሥራኤልና ዐረቦች ጦርነት ሳቢያ ፤ እሥራኤል በኃይል በያዘቻቸው የፍልስጤም ግዛቶች የሠፈራ መርኀ ግብሯን አለማጠፏ፣ የመካከለኛውን ምሥራቅ ውዝግብ በሰላም ድርድር ለመፍታት ፣ በየጊዜው የቀረቡ እቅዶችን ሁሉ መቅኖ እያሳጣ መቅረቱ የሚታወስ ነው። አዲስ የሰላም ድርድር ለመጀመር ፤የዩናይትድ እቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ያደረጉት ተደጋጋሚ ጥረት፤ በአንዳንድ አገላለጾች ፤ ፍልስጤማውያን ለውጥ እንዲደረግ በመጠየቃቸው፤ ሙሉ በሙሉ የሚሠምር አልመሰለም ። እንደ ዩናይትድ እስቴትስ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ የቆየው የአውሮፓው ኅብረት ፤ በሰላሙ ሂደት መጓተት ፤ እሥራኤልንና ፍልስጤማውያንን ፤ በይበልጥም እሥራኤልን ወቅሷል። ግርማው አሻግሬ ዝርዝር ዘገባ
ግርማው አሻግሬ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ