የእሥራኤል ምርጫ ውጤት ፤ ሥጋትና ተስፋው | ዓለም | DW | 22.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የእሥራኤል ምርጫ ውጤት ፤ ሥጋትና ተስፋው

ዘመናዊቷ እሥራኤል፣ እ ጎ አ ግንቦት 14 ቀን 1948 ዓ ም ፤ መንግሥት ከመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ ፣ ከፍልስጤማውያንና ከዐረብ መንግሥታት ጋር ተደጋጋሚ ጦርነቶች ተካሂደው እንደነበረ የሚታወስ ነው።የኦስሎውን ስምምነት ጨምሮ በጠቅላላ ከ 14 የማያንሱ

ዐበይት ስብሰባዎችም ፣ ስምምነቶችም ተደርገዋል። ያም ሆኖ ግን ፣ ፍጥጫው፣ ግጭቱ ፣ የሰላም እጦቱ እንዳለ ነው። ለእሥራኤልና ለፍልስጤማውያን ውዝግብ ሰላም በመሻቱ ሂደት ፤ የእሥራኤል ጠ/ሚንስትር ይስሐቅ ራቢን ጭምር መስዋእት ቢሆኑም ፤ እስካሁን ሁለቱን ወገኖች ለዘላቂ ሰላም የሚያበቃ መፍትኄ አልተገኘም። ምዕራባውያን የእሥራኤል ወዳጅ መንግሥታት ጭምር የተስማሙበት ፣ በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኘው ከእሥራኤል ጎን ፤ የፍልስጤም መንግሥት እንዲቋቋም የሚለው የመፍትኄ ሐሳብ፣ አሁን እንደገና በተመረጡት የእሥራኤል ጠ/ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በምርጫ ዋዜማ ላይ «አይሞከርም!» የሚል ቃል መሠንዘራቸው አላስደነገጠም ፤ አላሳሰበም አይባልም። ከዚህ በመነሣት ፣እሥራኤል፤ ፍልስጤማውን፤ ባጠቃላይ ምንጊዜም ሰላም እንደጠማው የሚገኘውን መካከለኛውን ምሥራቅ ምን ያጋጥመው ይሆን?

ተክሌ የኋላ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች