የኤድስ ስርጭት በዓለም ዙሪያና በኢትዮጵያ20 ኅዳር 2000ዓርብ፣ ኅዳር 20 2000ከሰሀራ በታች በሚገኙ አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት አሁን የኤድስ ስርጭት በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ ነው ። ሆኖም በአንዳንድ ሀገራት ለውጥ አልታየም ።https://p.dw.com/p/E0mkበኤድስ ወላጅ አልባ የሆነ ህፃንምስል APማስታወቂያ UNAIDS እንዳስታወቀው በአሁኑ ሰዓት በዓለም ዙሪያ ኤድስን ከሚያስከትለው ኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሶስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ደርሷል ። ድርጅቱ ዘንድሮ እንደገና አስተካክሎ ያወጣው ይህ አሀዝ ካለፈው ዓመቱ ጋር ሲነፃፀር በሰባት ሚሊዮን ገደማ ዝቅ ያለ ነው ።