1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤኮኖሚ ቀውስ እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥቅምት 17 2017

በተለያዩ ግጭቶች እና ጦርነቶች ውስጥ ለዓመታት በተከታታይ በዘለቀችው ኢትዮጵያ የኑሮ ውድነቱ ብዙዎችን እያማረረ ነው ። እንደ ተመድ የሐምሌ ወር መረጃ፦ ከ133 ሚሊዮን በላይ ነዋሪ ባላት ኢትዮጵያ አብዛኛው ነዋሪ የዕለት ኑሮውን ለመግፋት እንኳ እጅግ መቸገሩን ሲገልጥ ይደመጣል ።

https://p.dw.com/p/4mFNr
ዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF)
ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ግፊት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ብር ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሪ ተመን በፊት ከነበረው አዳክሟልምስል SNA/IMAGO

በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ለውጥ ወይንስ የፖሊሲ ማሻሻያ?

በተለያዩ ግጭቶች እና ጦርነቶች ውስጥ ለዓመታት በተከታታይ በዘለቀችው  ኢትዮጵያ የኑሮ ውድነቱ ብዙዎችን እያማረረ ነው ። እንደ ተመድ የሐምሌ ወር መረጃ፦ ከ133 ሚሊዮን በላይ ነዋሪ ባላት ኢትዮጵያ አብዛኛው ነዋሪ የዕለት ኑሮውን ለመግፋት እንኳ እጅግ መቸገሩን ሲገልጥ ይደመጣል ። መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይነገራል ።

ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ግፊት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ብር ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሪ ተመን በፊት ከነበረው አዳክሟል ።  ለዘመናት በመንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ስር የነበረው አንጋፋው እና ትርፋማ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚገልጠው ኢትዮ-ቴሌኮም በበኩሉ የመጀመሪያ የአክሲዮን ሽያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል ። የኩባንያውን 10 በመቶ ድርሻ ለኢትዮጵያውያን በሽያጭ እንደሚተላለፍም ተገልጧል ። እነዚህና ሌሎች ውሳኔዎች የሀገሪቱን ኤኮኖሚ ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች መሆናቸውን መንግስት ይናገራል ።

እንዲያም ሁኖ፦  በኢትዮጵያ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ መናር እና የኑሮ ውድነት ማቆሚያ ያለው አልመሰለም ። አዲሱ ዓመት 2017 እንደገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት፣   ኢትዮ ቴሌኮም፣  የውኃ እና ፍሳሽ   ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ዐሳውቀዋል ። ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውም ማኅበረሰቡን እጅግ አስጨንቆታል ። ደመወዝ ጭማሪ ቢደረግም ከኑሮ ውድነቱ ጋር የሚጣጣም እንዳልሆነ ብዙዎች ይናገራሉ ። «የኤኮኖሚ ቀውስ እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ» የዛሬው እንወያይ መሰናዶ ዐቢይ ትኩረት ነው ። በውይይቱ 4 እንግዶች ተሳታፊ ናቸው ።

1-ኤሚሬተስ ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ፦የኤኮኖሚክስ ምሁር፥ በጡረታ ላይ ይገኛሉ፥ በርካታ መጽሓፍትን እና መጣጥፎችን ለንባብ አብቅተዋል  ።

2-አብዱልመናን መሃመድ (ዶ/ር) የምጣኔ ሃብት ባለሙያ፥ በኢትዮጵያ ኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ዘርፍ የመመረቂያ ጽሑፍ አጥንተው ያቀረቡ እና ጥናት በማካሄድ ላይ ያሉ፤ እንግሊዝ ሀገር በፋይናንስ ሞያ ተሰማርተዋል ።

የንጹሕ መጠጥውኃ አቅርቦት ኢትዮጵያ ውስጥ በበርካታ አካባቢዎች እጅግ አንገብጋቢ ችግር ነው
ኤኮኖሚያቸው ባደጉ ሃገራት ውስጥ ዋነኛ ችግር የማይባለው የንጹሕ መጠጥውኃ አቅርቦት ኢትዮጵያ ውስጥ በበርካታ አካባቢዎች እጅግ አንገብጋቢ ችግር ነውምስል Ed Ram/Getty Images

3-አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን፦ የፖለቲካል ኤኮኖሚ ተንታኝ እና የዲመቴ መጽሐፍ ደራሲ

4- ዓማንይሁን ሲሣይ፦ የንግድ እና ኤኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ናቸው ።

ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ማዕቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።

በዚህ ውይይት መንግስት ተሳታፊ እንዲመድብ  ለጠቅላይ ሚንሥትር ጽ/ቤት  ይፋዊ የኢሜል ግብዣ ብንልክም ውይይቱን እስካደረግንበት ጊዜ ድረስ ምላሽ አላገኘንም ። የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ማኅበር ከፍተኛ አመራር በሥራ ጫና ምክንያት መሳተፍ እንደማይችሉ ገልጠዋል ። ሆኖም የማኅበሩ የማክሮ ኤኮኖሚ አንድ ባለሞያ ግን መልሰን እንድንደውል ከገለጡ በኋላ ለስልክ ጥሪያችንም ሆኑ ለተደጋጋሚ የጽሑፍ መልእክታችን ምላሽ አልሰጡንም ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ