የኤስ.ኤ.ቢ.ሲ ውሳኔና የደረሰው ትዕዛዝ | አፍሪቃ | DW | 12.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኤስ.ኤ.ቢ.ሲ ውሳኔና የደረሰው ትዕዛዝ

በእንግሊዘኛው ምህፃር ICASA የሚባለው ገለልተኛው የደቡብ አፍሪቃ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ባለሥልጣን ፣ SABC በጎርጎሮሳዊው ግንቦት 2016 ባወጣው መግለጫ በተቃውሞዎች ወቅት በመንግሥት ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጥፋቶችን የሚያሳዩ ምስሎችን ላለማስተላለፍ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ነው ትዕዛዝ የሰጠው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:16

የኤስ .ኤ.ቢ.ሲ ውሳኔና የደረሰው ትዕዛዝየደቡብ አፍሪቃ መገናኛ ብዙሃን ኮርፖሬሽን በእንግሊዘኛ ምህጻሩ (SABC) እጅግ አስከፊ ተቃውሞዎችን የሚያሳዩ ምስሎችን አየር ላይ ላለማውጣት ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ትናንት ትዕዛዝ ደርሶታል ።በእንግሊዘኛው ምህፃር ICASA የሚባለው ገለልተኛው የደቡብ አፍሪቃ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ባለሥልጣን ፣ SABC በጎርጎሮሳዊው ግንቦት 2016 ባወጣው መግለጫ በተቃውሞዎች ወቅት በመንግሥት ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጥፋቶችን የሚያሳዩ ምስሎችን ላለማስተላለፍ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ነው ትዕዛዝ የሰጠው ። ውሳኔውን ያሳለፈው ስሜታዊ ተቃውሞዎች ላለማበረታት መሆኑን ያሳወቀው SABC የተጫነበትን ትዕዛዝ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው አስታውቋል ። ስለ SABC ውሳኔ እና ድርጅቱ ስለደረሰው ትዕዛዝ ጆሃንስበርግ የሚገኘውን ጋዜጠኛ መላኩ አየለን ስቱድዮ ከመግባቱ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
መላኩ አየለ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic