የኤርትራ ፕሬዚደንት የዩጋንዳ ጉብኝት እና አንደምታው | ኢትዮጵያ | DW | 17.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኤርትራ ፕሬዚደንት የዩጋንዳ ጉብኝት እና አንደምታው

ዩጋንዳ ትናንት የሶስት ቀናት ይፋ ጉብኝት የጀመሩት የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች መካከል ግንኙነቱን ለማጠናከር ያካባቢው መሪዎች በየጊዜው እየተገናኙ እንዲወያዩ ጥሪ ማቅረባቸውን የዩጋንዳ ፕሬዚደንታዊ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ አስታወቁ።

default

ኤርትራዊው ፕሬዚደንት በመዲናይቱ ካምፓላ ከዩጋንዳዊው አቻቸው ዮዌሪ ሙሴቬኒ ጋ ያካሄዱት ውይይት ባካባቢው ስልታዊ እና ፖለቲካዊ፡ እንዲሁም የሁለቱ ሀገሮች የጋራ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። የዩጋንዳ ፕሬዚደንት በተለይ ከአል ቓይዳ ጋ ግንኙነት አለው፡ ኤርትራም ትረዳዋለች የሚባለው የአሸባብ ቡድን በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ አምና ጥቃት ጥሎ በርካቶችን ከገደለ በኋላ አሁን የኤርትራውን ርዕሰ ብሄር ወደ ሀገራቸው መጋበዛቸው ብዙ ያካባቢ ታዛቢዎችን አስገርሞዋል። የግብዣው ዓላማ ምን ሊሆን ይችላል? አርያም ተክሌ ያነጋገረቻቸው በፕሪቶርያ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የጸጥታ ጥበቃ ጥናት ተቋም የምስራቅ አፍሪቃ ተመራማሪ ዶክተር ኤማኑዌል ኪሳንጋኒ ቀጣዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic