1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ ክስና የመንግስት ምላሽ

ረቡዕ፣ ሰኔ 2 2013

በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ጊዜያዊ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው መሰየማቸውን የሚገልጹት አቶ ለሚ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ጦሩ ቀደም ሲል በምዕራብ ኦሮሚያ አሁን ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ መረጃውን መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል።

https://p.dw.com/p/3uf7a
 Logo Oromo Liberation Front

የኦነግ ክስና የመንግስት ምላሽ

በአቶ ዳውድ ኢብሳ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ.) ሰሞኑን በተደጋጋሚ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ የኤርትራ ጦር ሰራዊት በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ ብሏል። በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ጊዜያዊ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው መሰየማቸውን የሚገልጹት አቶ ለሚ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ጦሩ ቀደም ሲል በምዕራብ ኦሮሚያ አሁን ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ መረጃውን መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል። ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ