የኤርትራ የሠብአዊ መብት ይዞታና ተመድ | አፍሪቃ | DW | 07.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኤርትራ የሠብአዊ መብት ይዞታና ተመድ

ኮሚሽኑ-የሥራ ዉጤቱን ነገ ለመገናኛ ዘዴዎች ይፋ ካደረገ በኋላ ሰኔ 14፤ 2008 ለተባበሩት መንግስታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት ዝርዝር ግኝቱን ያቀርባል።ዉጪ የሚኖሩ ኤርትራዉያን ዘገባዉ ይፋ ከሚሆንበት ከነገ ጀምሮ ዤንቭ ዉስጥ የአደባባይ ሠልፍና ለማድረግ እየተዘጋጁ ነዉ-

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:08

የኤርትራ የሠብአዊ መብት ይዞታና ተመድ

የኤርትራን የሠብአዊ መብት ይዞታን የሚያጠናዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪ ኮሚሽን ሁለተኛ የጥናት ዉጤቱን ነገ ዤኔቭ ዉስጥ ይፋ ያደርጋል።ኮሚሽኑ ባለፈዉ ዓመት ባወጣዉ የመጀመሪያዉ የጥናት ዉጤቱ ኤርትራ ዉስጥ ከፍተኛ የሠብአዊ መብት ጥሰት እንደሚፈፀም አስታዉቆ ነበር።ዉጪ የሚኖሩ የኤርትራ የሰብአቂ መብት አቀንቃኞች እንደሚሉት ዓለም አቀፉ ድርጅት ነገ የሚያወጣዉ ዘገባ ኤርትራ ዉስጥ የሚፈፀመዉን ግፍ በትክክል የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት።የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን ዘገባዉ ይፋ እስኪሆን ድረስ አስተያየት አንሰጥም ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት የሠየመዉ ኮሚሽን ሰወስት አባላት አሉት።የአዉስትሬሊያ፤ የጋና እና የሞሪሸስ ዜጎች ናቸዉ።ሰወስቱም በዓለም አቀፉ ድርጅት መግለጫ መሠረት ገለልተኛ ባለሙያዎች ናቸዉ።ዓመት በፈጀ ጥናታቸዉ ያገኙትን መረጃ ነገ-ለመገናኛ ዘዴዎች ይፋ ያደርጋሉ።

የመረጃዉ ይዘት በርግጥ እስከነገ ሚስጥር ነዉ።ኤርትራዊዉ የሕግ ምሁር እና የሠብአዊ መብት ተሟጋች ዶክተር ዳንኤል ረዘነ እንደሚሉት ግን ኮሚሽኑ ባለፈዉ ዓመት የሰጠዉን ፍንጭ ዘንድሮ በግልፅ ያጠናክራል ብለዉ

ይጠብቃሉ።በዶክተር ዳንኤል እምነት ኤርትራ ዉስጥ የሚፈፀመዉ የሠብአዊ መብት ጥሰት ከጊዜ እየከፋ፤ጭካኔዉ እየበረታ፤ የሕዝቡ ስቃይ ማብቂያ የለሽ እየመሠለ ነዉ።ይሕ ግፍ በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል መሆኑን በተደጋጋሚ አስታዉቀናል ባይ ናቸዉ-ዶክተር ዳንኤል።

የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት የኮሚሽኑ ዘገባ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙን ካረጋገጠ ወንጀሉን ፈፀሙ የሚባሉት ባለሥልጣናት በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስክ መከሰስ የሚደርስ እርምጃ ይጠብቃቸዋል።የተባበሩት መንግሥታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት፤ የመርማሪ ኮሚሽኑን ዘመነ-ሥልጣን ባንድ ዓመት እንዲራዘም የወሰነዉ ባለፈዉ ዓመት ነበር።በዚሕ አንድ ዓመት ዉጥስ ኮሚሽኑ ኤርትራ ዉስጥ ሆንተብለዉ የሚፈፀሙ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶችን፤ ደረጃቸዉንና የበዳዮችን ማንነት በግልፅ እንዲያጣራ ሐላፊነት ተሰጥቶታል።

ኮሚሽኑ-የሥራ ዉጤቱን ነገ ለመገናኛ ዘዴዎች ይፋ ካደረገ በኋላ ሰኔ 14፤ 2008 ለተባበሩት መንግስታት የሠብአዊ መብት ምክር ቤት

ዝርዝር ግኝቱን ያቀርባል።ዉጪ የሚኖሩ ኤርትራዉያን ዘገባዉ ይፋ ከሚሆንበት ከነገ ጀምሮ ዤንቭ ዉስጥ የአደባባይ ሠልፍና ለማድረግ እየተዘጋጁ ነዉ-እንደ ዶክተር ዳንኤል እንዳሉት።

የኤርትራ መንግስት ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ዛሬ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም።በስልክ ካነጋገርናቸዉ ባለሥልጣናት አንዱ፤«ዘገባዉ ከወጣ በኋላ መንግሥታቸዉ ሥለጉዳዩ ይፋ መግለጫ ያወጣል» ሲሉ ሌለኛዉ ባለሥልጣን ግን አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic