የኤርትራ ወጣቶች | አፍሪቃ | DW | 16.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኤርትራ ወጣቶች

ብሔርተኝነትን መግለፅ ለኤርትራዉያን ወጣቶች የሚመጣ ችግርን መከላከያ ጥሩ ሥልት ነዉ።ሌላ ቢሎ መዘዙ ሌላ ነዉ።አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ትንሽ ሐገር እራሷን ከተቀረዉ ዓለም ዘግታለች።ከሠላሳ ዓመት ጦርነት በሕዋላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ ነፃነትዋን በይፋ ያወጀችዉ በ1985 ነዉ።

Blick über Asmara.jpg Blick über die Häuser von Asmara vom Turm der Kathedrale aus gesehen. Im Vordergrund die Independence Avenue, aufgenommen 1997.

አሥመራ


ኤርትራ ወጣት ሐገር ናት።ወጣት የሚያሰኛት ከብዙዎቹ የአፍሪቃ ሐገራት ዘግይታ ነፃ በመወጣትዋ ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ ሕዝቧ ከግማሽ የሚበልጡት እድሜያቸዉ ከአስራ-አራት ዓመት በታች ያለ ወጣቶች በመሆናቸዉ ነዉ።ሁሉም ወጣቶች ብሔራዊ ዉትድርና አገልግሎት መስጠት ግዴታቸዉ ነዉ።የአገልግሎቱ ዘመን ገደብ ላይኖረዉ ይችላል።ብዙዎቹ ብሔራዊ አገልግሎቱን ሽሽት ሕይወት እስከ ማሳጣት የሚደርስ የስደት ጉዞን ይጋፈጣሉ።ባሁኑ ሰዓት አንድ ሚሊዮን ኤርትራዉያን በስደት ይኖራሉ።ከሐገሪቱ ሃያ-በመቶ ያሕሉ ማለት ነዉ።እዚያዉ ያሉት ግን፥ አንቲየ ዲይክሃንዝ እንደዘገበችዉ ብዙ ጊዜ ሥለ ሐገራቸዉ የሚናገሩት ጥሩ ጥሩዉን ነዉ።የዲክሐንዝን ዘገባ ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

አስመራ።ልጆች ይጫወታሉ።ወጣቶች ይመለከታሉ።ከመጫወቻዉ ሜዳ ወደ አንደኛዉ አቅጣጫ ሲመለከቱ በኢጣሊያ ቅኝ አገዛዝ ዘመን የተገነቡትን ጨምሮ ማራኪ ሕንፃዎች፥ ያማሩ ቤቶች (ደመቅ ያሉ) መደብሮች ይታያሉ።በተቃራኒዉ አቅጣጫ ተቃራኒዉን። የደከሙ፥ የተወነካከሩ ቤቶች- የድሆች መንደር።ልጆቹም አዋቂዎቹም እዚያ ይኖራሉ።ጋዜጠኛዋ አስተያየት እንዲሰጧት ጠየቀቻቸዉ።-አዋቂዎቹን መልስ ግን የለም።

ኤርትራ ዉስጥ የሚያስቡትን መናገር አደገኛ ሊሆን ይችላል።የሚሰማቸዉን የተናገሩ ብዙዎች ዘብጥያ ወርደዋል።ከብዙ ማግባባት፥ ከርስ በርስ መደፋፈጥ፥ በኋላ አንዱ ተነፈሰ።

Displaced Eritreans receive blankets at the Dibarwa secondary school, 35 kilometers (22 miles) south of Asmara, Thursday, June 8, 2000. The school shelters some 54,000 people displaced by fighting between Eritrea and Ethiopia. Eritrea acknowledged for the first time that it was asking resident Ethiopians to move into camps for their own protection. (AP Photo/Jean-Marc Bouju)

ኤርትራዉያን ሥደተኞች«ጥሩ፥ ጥሩ፥ እንዴት ነሕ።» እንደማለት ነዉ።በቃ።እንደሱ ብጤ ወጣት ወንዶች ሥለ ወደፊት ሕይወታቸዉ ሠፊ ዕቅድ የላቸዉም።ምናልባት «ማግባት፥ ልጅ መዉለድ» ይላል ዳንኤል።እድሜ፥- አስራ-ዘጠኝ። ሥራ፥ መካኒክ።ደሞዝ ትንሽ።

«በቂ ገቢ አላገኝም።ግን ደሐ አይደለሁም።ሐብታምም አይደለሁም።»

ይላል ዳንኤል።ከሐገሩ ወጥቶ አያዉቅም።ኢንተርኔት አይጠቀምም።የዉጪ ጋዜጣ አያገኝም።ዓለሙም፥ ሐገሩም ኤርትራ ናት።

«የማዉቀዉ ኤርትራን ነዉ።እዚሕ በቋንቋዬ እግባባለሁ።ሐገሬ ነዉ።ሁሉም የተሟላ ባይሆንም በሐገሬ እኮራለሁ።»

ብሔርተኝነትን መግለፅ ለኤርትራዉያን ወጣቶች የሚመጣ ችግርን መከላከያ ጥሩ ሥልት ነዉ።ሌላ ቢሎ መዘዙ ሌላ ነዉ።አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ትንሽ ሐገር እራሷን ከተቀረዉ ዓለም ዘግታለች።ከሠላሳ ዓመት ጦርነት በሕዋላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ ነፃነትዋን በይፋ ያወጀችዉ በ1985 ነዉ።

«አንድ የተማርነዉ ነገር፥ ሐገር ከመገንባት አኳያ ሲታይ ሃያ-ዓመት ትንሽ መሆኑን ነዉ።»

ይላሉ የፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂ ልዩ አማካሪ የማነ ገብረ አብ። መንግሥት ዜጎቹ ሁሉ ያለምንም ማንገራገር እንዲገዙለት ይፈልጋል።ሰበቡ ኢትዮጵያ ታሰጋናለች የሚል ነዉ።ማብቂያ ያጣዉ የብሔራዊ ዉትድርና አገልግሎት ምክንያትም ይኸዉ ነዉ።ከጥቂት ወራት በፊት ግን አገዛዙን በመቃወም መፈንቅለ መንግሥት መሞከሩ በሰፊዉ ተነግሮ ነበር።የአስመራ መንገዶችም ታንኮች ሲንከባለሉባቸዉ ታይተዋል። ቴሌቪዥን ጣቢያዉ ስርጭት አቋርጦም ነበር።

አቶ የማነ ግን መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መደረጉን አይቀበሉትም።የብዙዎቹ ችግሮች ምክያንትም እንደ አቶ የማነ ጦርነቱ ነዉ።

«ከባድ ጉዳዮች ነበሩ።በጦርነቱ ምክንያት አስራ-ስምንት ወራት የሚቆይ የብሔራዊ አገልግሎት መርሐ-ግብር አለን።አንዳዶች ከአስራ-ስምንት ወር በላይም ቆይተዋል።ለረጅም ጊዜ ደሞዝ መጨመርም አልቻልንም።መፍትሔ የሚሹ ብዙ ጉዳዮች አሉ።መፍትሔ የሚያገኙት ግን አጠቃላይ ኤኮኖሚዉ ሲያድግ ነዉ።ይሕ ከምንሰራባቸዉ ነገሮች አንዱ ነዉ።ሌላዉ ከሕዝባችን ጋር በተሻለ መንገድ መቀራረብና ሐሳብ መለዋወጥ ነዉ።»

ገዢዉ ፓርቲ «ከሕዝብ ጋር መቀራረብ» ለሚለዉ መርሑ ወጣት አባላቱን አሠማርቷል።ሠላም ተክለ ማርያም አንዷ ነች።የሃያ-ሰባት ዓመቷ ወጣት ብሔራዊ አገልግሎት ግዳጅዋን ካጠናቀቀች በኋላ ከሥልጣኑ ማዕከል መንጠላጠል ችላለች።የአስመራ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቋ ከጥቂት ወራት በፊት ቻይና ደርሳ ተመልሳለች።በቅርቡ ደግሞ ወደ አዉሮጳ ትጓዛለች።

ወደ ሐገሯ እንደምትመለስ እስካሁን እርግጠኛ ነች።ሌሎች በሺ የሚቆጠሩ ወገኖቿ የሚሰደዱትም በፖለቲካ ምክንያት አይደለም ትላለች።

President of Eritrea Isaias Afewerki attends a news conference with European Commissioner for Development and Humanitarian Aid Louis Michel (not pictured) after their meeting at the European Commission headquarter in Brussels, Belgium, 04 May 2007. EPA/OLIVIER HOSLET +++(c) dpa - Report+++

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ«ታዉቂያለሽ? ብዙ አፍሪቃዉያን ዉጪ መሔድ የሚፈልጉት በኢኮኖሚ ቀዉስ ምክንያት ነዉ።የኢኮኖሚ ቀዉስ ነዉ፥ ወደ ዉጪ ተሰደን ቤተሰቦቻችንን መርዳት እንችላለን የሚል እምነት የሚያሳድረዉ።ከዚሕ ሌላ የፖለቲካም ሆነ ሌላ ችግር የለብንም።»

ኤርትራ ዉስጥ ሌላ ችግር መኖሩን መናገር ሌላ ችግር መጋበዝ ነዉ።ብዙዎቹ (መንግሥትን) ከመተቸት፥ ጀርመናዊቷ ጋዜጠኛ እንደታዘበችዉ፥ አፈን ዘግቶ መቀመጥን ይመርጣሉ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ