የኤርትራ አፋሮች ስሞታ | አፍሪቃ | DW | 13.09.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኤርትራ አፋሮች ስሞታ

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ በመባል የሚታወቀዉና ዋና መቀመጫዉን ኦትዋ ካናዳ ያደረገዉ ለተጨቆኑ የኤርትራ አፋር ሕዝቦች እና ራስን ለማስተዳደር መብት እንደሚታገል የሚገልፀዉ ድርጅት በሳምንቱ መጀመርያ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ስልታዊዉን የቡሬ ድንበር መክፈታቸዉ ጥሩ መሆኑን አስታዉቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:55

ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን መጠቀምዋን አንቃወምም

ኤርትራ ከጎረቤት ኢትዮጵያ ሰላም ስምምነት ላይ ደርሰዉ ጥሩ ግንኙነት ቢጀምሩም፤ በደል የደረሰበት የኤርትራ አፋር ሕዝብ አሁንም ጥያቄዉ አልተመለሰም ሲል የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ ስሞታዉን ገለፀ። የኤርትራ መንግሥትን የሚቃወመዉ ለተጨቆኑ የኤርትራ አፋር ሕዝቦች እንደሚታገል የሚገልፀዉ ድርጅት፤ ሃገራችን ጥለን የተሰደድን የኤርትራ አፋሮች አሁንም ወደ ሃገራችን ለመመለስ አደጋ ተጋርጦብናል ብሎአል።

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ በመባል የሚታወቀዉና ዋና መቀመጫዉን ኦትዋ ካናዳ ያደረገዉ ለተጨቆኑ የኤርትራ አፋር ሕዝቦች እና ራስን ለማስተዳደር መብት እንደሚታገል የሚገልፀዉ ድርጅት በሳምንቱ መጀመርያ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ስልታዊዉን የቡሬ ድንበር መክፈታቸዉ ጥሩ መሆኑን አስታዉቀዋል። ሆኖም ድርጅቱ አሁንም የኤርትራ አፍር ሕዝቦች ጥያቄ አልተመለሰም፤ ሲል ነዉ ስሞታዉን ያሰማዉ። የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ ቃል አቀባይ አቶ አሊ መሐመድ ኡመር እንደሚሉት፤ ድንበሩ ቢከፈትም በስደት ያሉ የኤርትራ አፋሮች አሁንም ወደ ሃገራቸዉ ለመመለስ ስጋት አለባቸዉ።             

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ ወደ 60ሺህ የኤርትራ አፋሮች በስደት እንደሚገኙ ይገልፃሉ ። የአሰብ ወደብ ዋንኛ ባለቤት የኤርትራ አፋር ሕዝቦች መሆኑን የተናገሩት ኢትዮጵያ መጠቀሙዋን አንቃወም ሲሉ የአፋር ብሔራዊ ጉባኤ ቃል አቀባይ ገልፀዋል።    

በኢትዮጵያ የሚገኙት የኤርትራ አፋር ስደተኞች በበኩላቸዉ የየቡሬ ድንበር መከፈትና አከፋፈቱ በብዥታ ዉስጥ እንደከተታቸዉ ይናገራሉ።  የሰመራ ከተማ አዋሳኝ በሆነችዉ ሎጊያ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብደላ ዓሊ መሐመድ እንደሚሉት ድንበሩ ተከፍቶአል ብንባልም፤ ስለአፋር እስተኞች ጉዳይ የተባለ ነገር ባለመኖሩ ወደ ሃገራችን ለመመለስ ስጋት ፈጥሮብናል፤ ።

በኤርትራ መንግሥት የተበደልን ሕዝቦች ስለሆንን ራሳችንን መብት ለማግኘት እንታገላለን ሲሉ የገለፁት የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ ቃል አቀባይ አሊ መሐመድ ኡመር ፤    የኤርትራ አፋር ሕዝብ ችግርን እንዴት ያዩታል ስንል ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ደብዳቤ መላካቸዉንና ድርጅታቸዉ ቀደም ሲልም ካናዳ ለሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ደብዳቤ አስገብቶ እንደነበር ተናግረዋል።  

የኤርትራ አፋር ጥያቄን ይዘን በኤርትራ መልስ እንዲሰጤን ወደ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረግነዉ የስልክ ጥሪ ሙከራ አልተሳካም ሙከራችንን ግን እንቀጥላለን  

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic