የኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎና የባለሙያ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 02.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎና የባለሙያ አስተያየት

የዘመቻዉ የጊዜ ገደብ የተሻረበት እዉነተኛ ምክንያት አቶ አብረሐም እንደሚያምኑት ፖለቲካዊ ነዉ።ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት የተረቀቀዉ ሕገ-መንግሥት በሥራ ላይ አልዋለም።ከጦርነቱ በሕዋላ ሕገ-መንግሥቱ ገቢር እንዲሆን የጠየቁ ባለሥልጣናትም ታስረዋል።

default

የኤርትራ መንግሥት የብሔራዊ አገልግሎት የዘመቻ ጊዜን ማራዘሙ ተገቢ እንዳልሆነ አንድ ኤርትራዊ የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሙያ አስታወቁ።በይፋ በሚታወቀዉ አዋጅ መሠረት ኤርትራዊ ወጣት አገልግሎት መስጠት የሚጠበቅበት ለአስራ-ስምንት ወራት ብቻ ነዉ።የኤርትራ መንግሥት ግን የተለያዩ ምክንያቶችን እየሰጠ የዘመቻዉን ጊዜ እያራዘመዉ ነዉ።የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሙያ አብረሐም ምሕረተዓብ እንደሚሉት ዘመቻዉን ለማራዘም የሚሰጠዉ ምክንያት ሕገ-ወጥ፥ ከእዉነት የራቀም ነዉ።ከሐገር የወጡ ኤርትራዉን ከየኤምባሲዉ ፓስፖርት ለማግኘት የክሕደት ፎርም እንዲፈርሙ መገደዳቸዉንም አቶ አብረሐም ተቃዉመዉታል። አቶ አብረሐምን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።


እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር በ1995 በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 82 አንቀፅ ሃያ-አንድ መሠረት የብሔራዊ አገልግሎት ዘማቹ በአመት ከመንፈቅ ጊዜ ዉስጥ አገልግሎቱን ያጠናቅቃል።ሐገሪቱ በአስቸኳይ አዋጅ ሥር፥ በጦርነት ወይም በክተት ላይ ካለች ግን የዘመቻዉ ጊዜ እንደሚራዘም አዋጁ ይደነግጋል።ይሕ ሁኔታ የነበረዉ የመብት ተሟጋችና የሕግ አዋቂ አብረሐም ምሕረተዓብ እንደሚሉት በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ግጭት ወቅት ነዉ።
ድምፅ
ኤርትራ ዉስጥ አሁን ጦርነት የለም የሚለዉን አስተያየት የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚስቴር ቃል አቀባይ አቶ ፍሰሐ ፅዮን ጴጥሮስም ይስማሙበታል።የዚያኑ ያክል ግን ሰላምም የለም ባይ ናችዉ-ቃል አቀባዩ።እና እንደ ቃል አቀባዩ የዘመቻዉ የጊዜ ገደብ መሻሩ ተገቢ ነዉ።አብረሐም ምሕረተዓብ እንደታዘቡት ግን ጦርነት በርግጥ የለም።ለአስር አመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አሰቸኳይ ሊሆን አይችልም።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ ከብዙ ሐገራት በተሻለ ሰላምና ፀጥታ የሰፈነባት መሆኗን በቅርቡ ለጋዜጠቾች ደጋግመዉ ገልጠዋል-ይላሉ አቶ አብረሐም።

Isaias Afewerki Präsident von Eritrea


ድምፅ
በዚሕም ምክንያት የቃል-አቀባይዩና የፕሬዝዳንት መግለጫ፥ የሚሆንና የሚባለዉም ይቃረናል።
የዘመቻዉ የጊዜ ገደብ የተሻረበት እዉነተኛ ምክንያት አቶ አብረሐም እንደሚያምኑት ፖለቲካዊ ነዉ።ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት የተረቀቀዉ ሕገ-መንግሥት በሥራ ላይ አልዋለም።ከጦርነቱ በሕዋላ ሕገ-መንግሥቱ ገቢር እንዲሆን የጠየቁ ባለሥልጣናትም ታስረዋል።ከዚያ በሕዋላ ሐገሪቱ የምትመራዉ ባዲስ አዋጅ ነዉ።ዋርሳ ይካዓሎ-በሚባል-አዋጅ።
ድምፅ

ገደብ አልባዉን ዘመቻ አቋርጠዉ ከሐገር የወጡ ኤርትራዉን ወጣቶች «መፀፀታቸዉን» ከገለፁ በየደረሰቡት ሐገር ከሚገኙ ኤምባሲዎች ፖስፖርት እንደሚያገኙ የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።ፖስፖርቱ የሚገኘዉ ግን አቶ አብረሐ እንደሚሉት አመልካቹ መፀፀቱን ሳይሆን ሐገር ከሐዲነኝ ብሎ፥ በተፈለገበት ጊዜ ተጠያቂ መሆኑን በፊርማዉ ሲያረጋግጥ ብቻ ነዉ።
ድምፅ
ቃመ፥ ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ