የኤርትራ ባለሥልጣን ጉብኝት ያሳሰባት ኔዘርላንድ | አፍሪቃ | DW | 13.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኤርትራ ባለሥልጣን ጉብኝት ያሳሰባት ኔዘርላንድ

በኤርትራ በስልጣን ላይ ካለዉ ሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ «PFDJ» ጋር ቅርብ ግንኙነት አለዉ የሚባለዉ የኤርትራ ወጣቶች ኮንግረስ ዓመታዊ ጉባዔዉን በኔዘርላንድ ሮተርዳም ከተማ በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገልጾአል። ኤርትራ ስደተኞች ኔዘርላንድ ውስጥ ከሶሪያውያን ቀጥለው በቁጥር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:02

የኔዘርላንድስ መንግሥት አቶ የማነ ከባለሥልጣን ጋር እንደማይገናኙም ብሎአል።

የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የፖለቲካ አማካሪ አቶ የማነ ገብርአብ በጉባዔዉ ለመገኘት እና ንግግር ለማድረግ ቀደም ብለዉ ባለፈዉ ሰኞ ሆላንድ መግባታቸዉ ታዉቋል። የኔዘርላንድ መንግሥት ግን በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በጥገኝነት በሚኖሩባት ሆላንድ አንድ የኤርትራ መንግሥት  ከፍተኛ ባለሥልጣን ለኤርትራዉያን ስብሰባ ለመገኘት ወደ ሆላንድ መምጣቱ ያሳሰበዉ መሆኑን ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል። አቶ የማነ ገብረ አብ የኤርትራ ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ለፍትኅ ከሐሙስ እስከ ሰኞ ለሚያኪያሂደው የወጣቶች ስብሰባ ኔዘርላንድ ውስጥ ንግግር እንደሚያደርጉ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የኔዘርላንድ መንግሥት የኤርትራ  የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንደሚያሳስበው አስታውቆ የኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሀገራቸውን ጥለው ለወጡ በርካታ ኤርትራውያን ንግግር ሊያደርጉ መኾናቸው ደግሞ «አሳፋሪ ነው» ብሏል። የአቶ የማነ «ገብረአብ ጉብኝት እንደ ግል ጉዳይ የሚታይ ነው» ያለው የኔዘርላንድስ መንግሥት አቶ የማነ ከማንኛውም ባለሥልጣን ጋር እንደማይገናኙ አስታውቋል። አቶ የማነ ወደ 650 ለሚሆኑ ኤርትራውያን ስደተኞች ንግግር እንደሚያደርጉ የሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ለፍትኅ የወጣቶች ንቅናቄ ማስታወቁን የዜና ወኪሉ አክሎ ጠቅሷል። የኤርትራ ስደተኞች ኔዘርላንድ ውስጥ ከሶሪያውያን ቀጥለው በቁጥር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። 
 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic