የኤርትራው ባለሥልጣንና ያልተጣራው ዘገባ፤ | አፍሪቃ | DW | 01.02.2013
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኤርትራው ባለሥልጣንና ያልተጣራው ዘገባ፤

ኤክስፕሬሲስን የተሰኘው የስዊድን ጋዜጣ ስለ ኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር አሊ አብዶ ከሀገር መኮብለል ያወጣው ዘገባ ያልተረጋገጠ ነው ተባለ። ዘጋቢው ከአቶ አሊ አብዶ ጋር የተነጋገረው በወንድማቸው ሳሌህ አማካይነት መሆኑን ጋዜጣው ሲናገር ግለሰቡ

ግን ዘገባውን አስተባብለዋል። በሌላ በኩል የአሊ አብዶ ከሀገር መውጣት ኤርትራ ውስጥ ለውጥ እየመጣ እንዳለ ማሳያ መሆኑም ተነግሯል።


የስዊድኑ ጋዜጣ ኤክስፕሬሲን ሰሞኑን ከአቶ አሊ አብዶ ጋር አደረግኩ ያለው ልዩ ቃለምልልስ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ተሰራጭቷል። ጋዜጣው ሀገር ለቀው ወጥተዋል ከተባሉ ከኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አሊ አብዱ ጋር በወንድማቸው ሳሌህ ዩሱፍ በኩል ቃለምልልስ ማድረጉን ዘግቧል። አቶ ሳለህ ዩኑስ ግን ፣ ገደብ ኒውስ በተሰኘው ድህረ ገጽ ላይ በሰጡት መልስ የጋዜጣው ዘገባ የተዛባ ነው ብለዋል።


ቃለምልልሱን ካደረገው የኤክስፕሬስን ጋዜጣ ዘጋቢ ካሴም ሃማዴ ጋር አቶ ሳሌህ ስለ አሊ አብዶ ዝርዝር ሁኔታ ሳይሆን ስለ ኤርትራ መንግስት ጠቅላላ ሁኔታ እንደተናገሩ ገልጸዋል። በቻተም ሃውስ የአፍሪቃ ቀንድ ፖሊቲካ ተንታኝ ጀይሰን ሞስሊም፤ጋዜጣው ቃለምልልሱ ቀጥታ ከአሊ አብዶ ጋር የተደረገ አስመስሎ አቅርቧል ይላሉ፤

«ቃለምልልሱ ቀጥታ ከአሊ አብዱ የመጡ በማስመሰል ነው የተዘገበው። ነገር ግን ከሳቸው ጋር አልተደረገም። መልስ ሰጪው ጋዜጠኛውን ከአሊ አብዱ ጋር ለማገኛነት እየሞከሩ ነበር። አሊ አብዱ ከሀገር መልቀቃቸው ግልጽ ይመስለኛል። ግን እንዴት እንደወጡና ዬት እንዳሉ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አይታይም።»ከሳምንት በፊት የኤርትራ መንግስት ወታደሮች አመጽው የኤርትራን ማስታወቂያ ሚኒስቴር ይዘው እንደነበር በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች ተነግሯል። አመጹ ከቆመ ወዲህም በኤርትራ የመንግስት ባለስልጣናት ከስልጣናቸው መባረራቸው ተስምቷል። የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ የአቶ አሊ አብዱ ከሀገር መሰደድ ዜና መነገር ከጀመረ ግን ሰነባብቷል። ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ አሊ አብዶ ከሀገር መውጣታቸው በኤርትራ ፖሊቲካ ለውጦች እየመጡ እንዳሉ ማሳያ ነው ይላሉ ጃይሰን ሞስሊ፤

«ከኤርትራ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ሀገር ለቆ በመውጣት አሊ አብዶ የመጀመሪያ ናቸው ብባል ስህተት አይመስልለኝም። የአሊ አብዶ ጉዳይ ባለፈው ዓመት በኤርትራ ውስጥ በታዩ ክስተቶች ጋር የተገናኘ አይደለም። ይህ የሚያመለክተው በኤርትራ መንግስት የፖለቲካ መሪዎች ውስጥ መከፋፈል እየተፈጠረ እንዳለ ነው። በኤርትርራ ነገሮች እየተቀየሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ትንሽ ምልክት ነው።»

ዶቸ ቬሌ ስለ አሊ አብዶ ከሀገር መውጣት ከኤርትራ መንግስት ወገን ምላሽ ለማግኘት የኤርትራ ፕሬዚዳንት ቃለ አቀባይ አቶ የማነ ገብረ መስቀልን በስልክ ቢጠይቅም ቃለ አቀባዩ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ገመቹ በቀለ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 01.02.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17Woi
 • ቀን 01.02.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17Woi