የኤርትራውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን | ኢትዮጵያ | DW | 23.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኤርትራውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን

ኤርትራውያን ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ውስጥ የተመድ በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ በማውገዝ ስላካሄዱት ዓለም ዓቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ትናንት አውስተናል ። በዚሁ በትናንትናው ዕለት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኤርትራውያንም ተመሳሳይ ሰልፍ አካሂደው ነበር ።

default

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ የማዕቀቡ ጠንሳሽ አሜሪካ ናት ሲሉ ከሰዋል ። በሌላም በኩል መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የዓለም ዓቀፍ ኤርትራውያን ወጣቶች ማሀበር የኤርትራ መንግስት ችግሮቹን ከመፍታት ይልቅ በሌሎች ላይ ማሳበብ ይመርጣል ሲል ወቅሶ የመንግስታቱን ድርጅት ውሳኔ የአሜሪካን ውሳኔ ማለት አግባብ አይደለም ብሏል ዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን ልኮልናል ። አበበ ፈለቀ ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ