የኤርትራውያን ስደተኞች ብሶትና የ« ዩኤንኤችሲአር » መልስ | ኢትዮጵያ | DW | 10.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኤርትራውያን ስደተኞች ብሶትና የ« ዩኤንኤችሲአር » መልስ

ማይ አይኒ በተባለው የስደተኞች ካምፕ ወደ ኢጣልያ ለመሻገር ሲሞክሩ ባለፈው ሳምንት የሞቱትን ኤርትራውያን ለማሰብ ባለፈው ቅዳሜ ማታ ስደተኞቹ ካዘጋጁት የሻማ ማብራት ስነስርዓት በኃላ ባካሄዱት ሰልፍ ብሶታቸውን ሲያሰሙ ነበር ።

ኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ሌላ 3 ተኛ አገር ለመሻገር ብዙ ዓመታት እንድንጠብቅ ይደረጋል ሲሉ አማረሩ ። ኤርትራውያኑ በነርሱ ቦታ ስደተኛ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ 3ተኛ አገር ይሄዳሉ የሚል ጥርጣሬም እንዳላቸው በአዲስ አበባ ለዶቼቬለ ወኪል አስታውቀዋል ። ማይ አይኒ በተባለው የስደተኞች ካምፕ ወደ ኢጣልያ ለመሻገር ሲሞክሩ ባለፈው ሳምንት የሞቱትን ኤርትራውያን ለማሰብ ባለፈው ቅዳሜ ማታ ስደተኞቹ ካዘጋጁት የሻማ ማብራት ስነስርዓት በኃላ ባካሄዱት ሰልፍ ብሶታቸውን ሲያሰሙ ነበር ። ወደ ግጭት በተቀየረው በዚሁ ሰልፉ የሰው ህይወት መጥፋቱንና በንብረትም ላይ ጥቃት መድረሱን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥት የስደተኖች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር የ« ዩኤንኤችሲአር » ቃል አቀባይ ለዴቼቬለ አስታውቀዋል ። ቃል አቀባዩ ስደተኞቹ ላነሷቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች