1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራዊዉ የቢኒያም ግርማይ የብስክሌት ዉድድር ድል

ማክሰኞ፣ ሰኔ 25 2016

ኢጣሊያና ፈረንሳይ ዉስጥ በሚደረገዉ የዘንድሮዉ የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ፉክክር ትናንት በተደረገዉ የሶስተኛ ቀን ዉድድር ኤርትራዊዉ ብስክሌት ጋላቢ ቢንያም ግርማይ አሸንፋል።ዘንድሮ የሚደረገዉ የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ዉድድር ለ111ኛ ጊዜ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4hmpT
በቱር ደ ፍራንስ የዉድድር ታሪክ አንድ ጥቁር አፍሪቃዊ ድል ሲያደርግ ቢኒያም የመጀመሪያዉ ነዉ
ኤርትራዊዉ ብስክሌት ጋላቢ ቢኒያም ግርማይ በሶስተኛዉ ዙር የቱር ደ ፍራንስ ዉድድር ድል አድርጎ ሲገባምስል Daniel Cole/AP/picture alliance

የኤርትራዊዉ የቢኒያም ግርማይ የብስክሌት ዉድድር ድል

 

ኢጣሊያና ፈረንሳይ ዉስጥ በሚደረገዉ የዘንድሮዉ የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ፉክክር ትናንት በተደረገዉ የሶስተኛ ቀን ዉድድር ኤርትራዊዉ ብስክሌት ጋላቢ ቢንያም ግርማይ አሸንፋል።

ዘንድሮ የሚደረገዉ የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ዉድድር  ለ111ኛ ጊዜ ነዉ።ቢንያም ያሸነፈዉ ከብዙ ዙሮች  የትናንቱን ወይም ሶስተኛዉን ዙር ነዉ።እንደ ግሪግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ1903 የተጀመረዉ ዉድድር ዘንድሮ ሲደረግ ለ111ኛ ጊዜ ነዉ።

አንድ ጥቁር አፍሪቃዊ ብስክሌት ጋላቢ ሲያሸንፍ ደግሞ በዉድድሩ ታሪክ ቢኒያም የመጀመሪያዉ ነዉ።የ24 ዓመቱ ወጣት የትናንቱን ድል ለመላዉ አፍሪቃ መታሰቢያነት ሰጥቷል።

 ኃይማኖት ጥሩነሕን 

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር