የኤርትራና የጅቡቲ ዉዝግብና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት | ኢትዮጵያ | DW | 02.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኤርትራና የጅቡቲ ዉዝግብና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እንደሚሉት ግን የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ መንግሥት ላይ አስገዳጅ ዉሳኔ ማሳለፍ አለበት

default

ዋና ፀሐፊ ፓን

ኤርትራ በሐይል ይዛዋለች ከሚባለዉ የጅቡቲ ግዛት ለቅቃ-አለመዉጣትዋን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አስታወቁ።ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን ከትናንት በስቲያ ለፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በፃፉት ደብዳቤ እንዳሉት ኤርትራ የጅቡቲን ግዛት እንድትለቅ ምክር ቤቱ ባለፈዉ ጥር ያሳለፈዉን ዉሳኔ አላከበረችም።የኤርትራ የያዝኩትም የተያዘብኝም ግዛት የለም ባይ ናት።ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እንደሚሉት ግን የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ መንግሥት ላይ አስገዳጅ ዉሳኔ ማሳለፍ አለበት።አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።