የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ዕቅድና የህዝብ ቅሬታ | ኢትዮጵያ | DW | 17.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ዕቅድና የህዝብ ቅሬታ

የኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከጅቡቲ በመጀመር ከመጪው ሀምሌ ወር አንስቶ ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል የመሸጥ ዕቅድ አለው። ህዝቡ ግን በኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ችግር ውስጥ እንደሆነ ይናገራል።

default

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢትዮዽያ መንግስት የኤሌክትሪክ ሃይል ለጎረቤት ሀገራት የመሽጥ እቅድ እንዳለው በተደጋጋሚ ይገልጻል። ይሁንና በእስከአሁን የመስመር ዝርጋታ ከማከናወን ያለፈ ሽያጭ እንዳልጀመረ አስታውቋል። ከመጪው ሀምሌ ወር ጀምሮ ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን የኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለዶቸ ቬሌ ገልጿል። ለዚህም ወደጅቡቲ የመስመር ዝርጋታው ተጠናቆ ለመረካከብ በዝግጅት ላይ እንደሆነም ኮርፖሬሽኑ ጨምሮ አስታውቋል። በሌላ በኩል በኢትዮዽያ ህብረተሰቡ በክፍተኛ የሃይል እጥረት ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ለጣቢያችን በሚላኩ የተለያዩ መልዕክቶች አማካኝነት ለመረዳት ችለናል። በኑሮ ውድነቱ ላይ የሃይል መቋረጥ ተደርቦ መኖር ከማንችልበት ደረጃ ላይ እንገኛለን ይላሉ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች። መሳይ መኮንን ሁለቱንም ወገኖች አግኝቷቸው ስለሁኔታው ጠይቋቸዋል። ከነዋሪው አስተያየት በመጀመር ዘገባው ይቀጥላል።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic