የኢጣልያ ፕሬዚደንት የድል ሐውልት ጉብኝት | ኢትዮጵያ | DW | 15.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢጣልያ ፕሬዚደንት የድል ሐውልት ጉብኝት

የኢጣልያ ፕሬዚደንት ሴርጂዮ ማታሬላ ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ በጀመሩት የአምስት ቀን ጉብኝታቸው ዛሬ በአዲስ አበባ በአራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:02
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:02 ደቂቃ

ፕሬዚደንት ማታሬላ በአራት ኪሎ

ከፋሺስት ኢጣልያ ጋር ከተፋለሙት መካከል በሕይወት ያሉት አርበኞች በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ በመገኘት ለኢጣልያዊው ርዕሰ ብሔር በሰልፍ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ኢጣልያዊው ፕሬዚደንትም የእያንዳንዱን አርበኛ እጅ በመጨበጥ ሰላምታ ሰጥተዋቸዋል። አንድ የኢጣልያ ፕሬዚደንት ኢትዮጵያን ሲጎበኝ ማታሬላ ሁለተኛው ናቸው። እንደሚታወሰው፣ የቀድሞው ፕሬዚደንት ኦስካር ልዊጂ ስካልፋሮ እጎአ ህዳር ፣ 1997 ዓም ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic