የኢጣልያ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለስደተኞች ያወጡት እቅድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 17.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኢጣልያ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለስደተኞች ያወጡት እቅድ

ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ ስደተኞች ወደ ኢጣልያ መምጣት የሚያስችላቸው ሰብዓዊ ቪዛ የሚያገኙባቸውን ቢሮዎች በሞሮኮ በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ ለመክፈት አቅደዋል ።


የኢጣልያ የካቶሊክና የወንጌላውያን ፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያን በጎ አድራጊ ድርጅቶች ሰሜን አፍሪቃና መካከለኛው ምሥራቅ ና እና ምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኑ ስደተኞችን ከአደገኛ የባህር ጉዞ ለመታደግ ማቀዳቸው ተሰማ ። ድርጅቶቹ በባህር ጉዞ የሚደርስ የሞት አደጋን ለማስቀረት ከነዚህ ሃገራት ስደተኞችን በአውሮፕላን ወደ ኢጣልያ ለማጓጓዝ እንዳቀዱ የጀርመን ዜና አገልግሎት «ዴ ፔ አ» የጠቀሳቸው መንግሥታዊ ያልሆነው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ግብረ ሰናይ ድርጅት ሃላፊ ማርኮ ኢምፓግልያዞ ተናግረዋል ።በዚሁ መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሚሆኑ የመጀመሪያዎቹ ስደተኞችም እስከ ፊታችን ጥር አጋማሽ ኢጣልያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ ስደተኞችን ወደ ኢጣልያ መምጣት የሚያስችላቸው ሰብዓዊ ቪዛ የሚያገኙባቸውን ቢሮዎች በሞሮኮ በሊባኖስ እና በኢትዮጵያ ለመክፈት አቅደዋል ። የስደተኞቹን የጉዞ፣ የመስተንግዶ እና የቋንቋ ትምህርት ወጪ እንዲሁም ለተገን ጥያቄአቸው የሚያስፈልጋቸውን ህጋዊ ድጋፍ ድርጅቶቹ እንደሚሸፍኑም ተዘግቧል ። የሮሙን ወኪላችንን ተክለ እግዚ ገብረ እየሱስን ስለ እቅዱ አተገባበር ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ጠይቄዋለሁ ።
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic