የኢጣልያ የፖለቲካ ይዞታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኢጣልያ የፖለቲካ ይዞታ

ኤኮኖሚዋ የዕድገት እንቅሥቃሴ አላሳይ ብሎ፤ በሥራ አጦች መበራከትና በበጀት ዕዳ የተወጠረችው ኢጣልያ፤ እነዚህን ችግሮች መፍታት የሚችል የተደላደለ መንግሥት ማቆም አቅቷት ስትዋትት ከቆየች በኋላ ፣

ኤኮኖሚዋ የዕድገት እንቅሥቃሴ አላሳይ ብሎ፤ በሥራ አጦች መበራከትና በበጀት ዕዳ የተወጠረችው ኢጣልያ፤ እነዚህን ችግሮች መፍታት የሚችል የተደላደለ መንግሥት ማቆም አቅቷት ስትዋትት ከቆየች በኋላ ፣ በመጨረሻ በመኻል ቀኝ ፈለግ ተከታዩ ፓርቲና በመኻል ግራ ፈለግ ተከታዩ ፓርቲ ጥምረት ፣ የሀገርን ጥቅም ለማስቀደም የተመሠረተው በጠ/ሚንስትር ኤንሪኮ ሌታ የሚመራው መንግሥት ፣ ትናንት ለጥቂት ነው ከመፍረስ የዳነው። ይህም ሊሆን የቻለው ፣ የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ የፓርቲአቸውን ሰዎች አግባብተው ፣ በምክር ቤቱ ፤ ለሌታ ድጋፍ እንዳይሰጥ ያካሄዱት ዘመቻ፤ አንጀሊኖ አላፋኖ በተባሉት የራሳቸው ፓርቲ ባልደረባ መሪነት የቤርሉስኮኒ ሃሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው። የኢጣልያን ወቅታዊ ፖለቲካ በተመለከተ የብራሰልሱን ዘጋቢአችንን ገበያው ንጉሤን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic