የኢጣልያ ማሳሰቢያ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የኢጣልያ ማሳሰቢያ

የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት ለሃገራቸው ፓርላማ ባሰሙት ንግግር በሊቢያ ሰላም ለማውረድ በሚደረገው ጥረት ሃገሪቱ የመሪነቱን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆንዋን አስታውቀዋል ።


ኢጣልያ አውሮፓ ላይ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል ባለችው ራሱን የሶሪያና የኢራቅ እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው IS ላይ አፋጣኝ የተባበረ እርምጃ እዲወሰድ ጥሪ አቅርባለች ። የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት ለሃገራቸው ፓርላማ ባሰሙት ንግግር በሊቢያ ሰላም ለማውረድ በሚደረገው ጥረት ሃገሪቱ የመሪነቱን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆንዋን አስታውቀዋል ።IS ኢጣልያ ውስጥ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል በሚል ስጋት ጥብቅ የፀጥታ ጥበቃ እንደሚካሄድ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማስታወቃቸውን የሮሙ ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ የሱስ ዘግቧል ።
ተክለ እዝጊ ገብረ የሱስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ

Audios and videos on the topic