የኢጣሊያ ጦር ዘመቻና የማርሻል ሐፍጣር ትዕዛዝ | አፍሪቃ | DW | 03.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኢጣሊያ ጦር ዘመቻና የማርሻል ሐፍጣር ትዕዛዝ

የማርሻሉ ማስጠንቀቂያ የተሰማዉ፤ ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን ታድናለች የተባለች አንዲት የኢጣሊያ ቃኚ ጀልባ ባካባቢዉ ሊቢያ ጠረፍ ከደረሰች በኋላ ነዉ።የቀድሞዉ የሊቢያ ቅኝ ገዢ ኢጣሊያ ሊቢያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን የሚያድን ጦር እንድታዘምት የሐገሪቱ ምክር ቤት ትናንት ወስኗል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29

የኢጣሊያ ዘመቻና የኢፍጣር ማስጠንቀቂያ

ምሥራቃዊ ሊቢያን የሚቆጣጠረዉ ጦር አዛዥ ኸሊፋ ሐፍጣር ወደ ሊቢያ የባሕር ክልል ያለፍቃድ የሚገባ የዉጪ ጦርን እንደሚመቱ አስጠነቀቁ።ለራሳቸዉ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ያጠለቁት ሐፍጣር ዛሬ እንዳስታወቁት ጦራቸዉ በራስ ላኑፍ፤ጡብሩክ እና በትሪፖሊ በኩል የሚገባ የዉጪ ጦርን እንዲመታ ታዝዟል።የማርሻሉ ማስጠንቀቂያ የተሰማዉ፤ ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን ታድናለች የተባለች አንዲት የኢጣሊያ ቃኚ ጀልባ ባካባቢዉ ሊቢያ ጠረፍ ከደረሰች በኋላ ነዉ።የቀድሞዉ የሊቢያ ቅኝ ገዢ ኢጣሊያ ሊቢያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን የሚያድን ጦር እንድታዘምት የሐገሪቱ ምክር ቤት ትናንት ወስኗል።ሥለዘመቻዉ ዉሳኔና ዓላማ የሮም ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ተኽለእዝጊ ገብረእየሱስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች