የኢድ አልአድሃ አከባበርና ተቃውሞ | ኢትዮጵያ | DW | 26.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢድ አልአድሃ አከባበርና ተቃውሞ

ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በዓሉ በየዓመቱ እንደሚደረገዉ ስታዲዮም በተካሔደ ሥግደት ቢከበርም መንግሥት በሐይማኖታዊ ነፃነታችንን አፍኗል፥ መሪዎቻችንን አስሯል፥ ሐባሽ የተሰኘዉን ሐራጥቃ ይደግፋል፥ የሚሉ ምዕመናን ተቃዉሟቸዉን አሰምተዉበታል።

default

ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን የዘንድሮዉን በዓል ተቃዉሞ፥ ዉግዘት፥ አንዳድ ሥፍራ ደግሞ ግጭትና እስራት አጥልቶበት እንደዋለ አንዳድ ዘገባዎች ጠቁመዋል።ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በዓሉ በየዓመቱ እንደሚደረገዉ ስታዲዮም በተካሔደ ሥግደት ቢከበርም መንግሥት በሐይማኖታዊ ነፃነታችንን አፍኗል፥ መሪዎቻችንን አስሯል፥ ሐባሽ የተሰኘዉን ሐራጥቃ ይደግፋል፥ የሚሉ ምዕመናን ተቃዉሟቸዉን አሰምተዉበታል።ምዕመኑ ከስግደቱ በሕዋላ በተለይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያን ከብቦ ተቃዉሞን ሲያሰማ ነበር።አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ ደግሞ ምዕመናኑ ከታላቁ አንዋር መስጊድ አጠገብ እጅ ለእጅ ተያይዘዉ በመሰለፍ መንግሥት ያሰራቸዉን የሙስሊም ተወካዮች እንዲፈታና ሐይማኖታዊ ነፃነታቸዉን እንዲያከብር ጠይቀዋል።ሌሎች ምንጮች እንዳስታወቁት፥ ናዝሬትና ጂማን በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ሙስሊም የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አዉግዟል።በምዕመናኑና በፖሊስ መካካል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች መጎዳት፥ መቁሰላቸዉ ተገዝግቧል።ዶቸ ቬለ ዘገባዉን ከነፃ ምንጭ አላረጋገጠም። በአዲስ አበባ ስታድዮም በተካሄደው የዘንድሮው የኢድ አል አድሃ በአል አከባበር ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን እንደነገረን በስታድዮም የተገኘው ምዕመን ከፅሎት ስነስርአቱ በኋላ ብጫ ወረቀት በማዉጣት ተቃዉሞን ሲገልፅ፤ በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ ቴልቪዥን በማምራት ተቃውሞውን አሰምቷል። በአዲስ አበባ ስለበአሉ አከባበርና ከዚያም ስለተከለው ተቃውሞ ወኪላችንን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄርን ጠይቀናል ። አዲስ አበባ እና ደሴ ስለ ነበረዉ ሁኔታም የበአሉን ተካፋዮች አነጋግረናል ።

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ

Audios and videos on the topic