የኢዴፓ እና ኢሃን አመራሮች ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን ተቀላቀሉ | ኢትዮጵያ | DW | 29.01.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢዴፓ እና ኢሃን አመራሮች ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሰውነታቸው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዙት የኢዴፓ እና የኢሃን ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሙሉ አባላቶቻቸው ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን በአባልነት ተቀላቀሉ። ሕብር ኢትዮጵያ በቅርቡ የተመሠረተ እና በአቶ ግርማ በቀለ የሚመራ የፖለቲካ ፓርቲ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

የኢዴፓ እና ኢሃን አመራሮች ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሰውነታቸው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዙት የኢዴፓ እና የኢሃን ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሙሉ አባላቶቻቸው ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን በአባልነት ተቀላቀሉ።
ሕብር ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ያላቸውን እነዚህን አመራሮች በሙሉ አባልነት ሲቀበል ያላቸው ልምድ፣ እውቀትና ተሳትፎ ከፓርቲው በላይ ለሀገር ጠቃሚ መሆኑን እንደሚያምን ገልጿል።
የሁለቱ የቀድሞ ፓርቲዎች አመራሮች ሕብር ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው አብሮነት ያራምደው የነበረውን አቋም አሁንም እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic