የኢዜማ ጉባኤ በባሕር ዳር | ኢትዮጵያ | DW | 28.12.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢዜማ ጉባኤ በባሕር ዳር

በፓርቲው ውስጥ ተንካራ አመራሮችና ኢትዮጵያዊነት በውስጣቸው በመኖሩ በስድስት ወር ውስጥ ብቻ በ400 የምርጫ ወረዳዎች መድረስ መቻሉን የኢትዮጵያውን ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አስታወቀ። ፓርቲው ዛሬ ምርጫና ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር በባሕር ዳር ከተማ ባካሄደው ስብሰባ መክሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:05

« በስድስት ወር ውስጥ ብቻ በ400 የምርጫ ወረዳዎች መድረስ መቻሉን ገልጿል»

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ በባሕር ዳር ባደረገው ውይይት ኢትዮጵያ ቀዳሚ ነፃነቷን ያስከበረች የአፍሪካውያን ምሳሌ ብትሆንም አሁን አሁን የሕዝቦች በሰላም ውሎ መግባት ፈተና የሆነባት አገር አንደሆነች በውይይቱ ተነስቷል። የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዳሉት አገሪቱ አሁን በዲሞክራሲ እጦት ችግር ውስጥ ብትሆንም ብሩህ ተስፋ ግን ከፊቷ እንዳለ አመልክተዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ፓርቲቸው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ሰፊ የምርጫ ወረዳ መሸፈን መቻሉን የተናገሩት አቶ የሺዋስ ለዚህም በፓርቲው ውስጥ ጠንካራና ኢትዮጵያን የሚያስቀድሞ አመራሮች በመኖራቸው መሆኑን አመልክተዋል።

Äthiopien | ETHzema Partei Versammlung im Bahir Dar Amhara Region

የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ

በቀጣዩ ምርጫ የዴሞክራሲ መሰረት መጣል አንዳለበት የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ ለዚህም ሰላማዊ የምርጫ ሂደት፣ ምርጫውን ሊሸከም የሚችል ዲሞክራሲያዊ ተቋማት መዘርጋትና አማራጭ ፓርቲ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አቶ ንጉሴ ዳኛው የተባሉ የውይይቱ ተካፋይ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት በተናጠል መደራጀት አገሪቱን ቁልቁል ወስዷታል፣ አንድነትን በሚያጠናክሩ አደረጃጀቶች ህዝቡ መሰባሰብ አለበት ነው ያሉት፡፡ ወ/ሮ ገነት አሰፋ በበኩላቸው የተለያዩ የዓለም አገራትን ተሞክሮ በማንሳት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ብዛት ከጥንካሬ ይልቅ ድክመትን የሚያሳይ በመሆኑ ውህደት መፍጠር አለባቸው ብለዋል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 10 የፖለቲካ ድርጅቶችን በማዋሃድ በቅርቡ የተደራጅ የፖለቲካ ፓርቲ ነው፡፡  በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic