የኢንጋቢሬ ችሎት | አፍሪቃ | DW | 06.09.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኢንጋቢሬ ችሎት

የሩዋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሩዋንዳ ከአሸባሪዎች ጋር በማበር ና በሌሎችም ወንጀሎች ክስ በተመሰረተባቸው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቪክቷር ኢንጋቢሬ ላይ ነገ የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ። ኢንጋቢሪ የዘር ልዩነት በስፋት በመቀስቀስ እና እጎአ በ1994 በሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመካድም ተከሰዋል ።

የሩዋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሩዋንዳ ከአሸባሪዎች ጋር በማበር ና በሌሎችም ወንጀሎች ክስ በተመሰረተባቸው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቪክቷር ኢንጋቢሬ ላይ ነገ የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ። ኢንጋቢሪ የዘር ልዩነት በስፋት በመቀስቀስ እና እጎአ በ1994 በሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመካድም ተከሰዋል ። ደጋፊዎቻቸው ክሱ ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ይላሉ ። የዶቼቬለው

ቪክቷር ኢንጋቢሬ ከተሰደዱበት ከኔዘርላንድስ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት እጎአ በ 2010 አም ነበር ። ያኔ ወደ ሃገራቸው የገቡትም የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በምሃፃሩ FDU Inkingi የተባለውን ተቃዋሚ ፓርቲያቸውን ለማስመዝገብ ና በፕሬዝዳንታዊ ምርጫም ለመካፈል ነበር ። ይሁንና በዚያው አመት በመስከረም ወር ለሚካሄደው ምርጫ ፓርቲያቸውን ለማስመዝገብ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም ። ይልቁንም ኢንጋቢሬ በአሸባሪነት የተፈረጀውን የሩዋንዳ ነፃ አውጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በምህፃሩ FDRL የተባለውን ቡድን በገንዘብ ደግፈዋል ፣ የዘር ልዩነት ለማስፋፋት ቀስቅሰዋል እንዲሁም የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት ክደዋል ተብለው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረገ ። ኢንጊባራ በተለይ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ክደዋል ተብለው የተከሰሱት ሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ በገቡበት እለት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ መታሰቢያ በተሰራው ማዕከል ተገኝተው ባሰሙት በዚህ ንግግር ምክንያት ነበር ።

Rwandan opposition leader Victoire Ingabire , left, listens to her British defence counsel Iain Edwards, during her trial in Kigali, Rwanda Monday, Sept. 5 2011. Ingabire, an outspoken critic of President Paul Kagamea's regime, is charged with allegations of providing financial support to a terrorist group, causing state security and formenting ethnic divisions. (Foto:Shant Fabricatorian/AP/dapd)

ኢንጋባሪና ጠበቃቸው ኤድዋርድስ

« ሃገሪቱ ወደ ብሔራዊ እርቅ የሚያመራ ውጤታማ የፖለቲካ መርህ የላትም ። በዚህ የመታሰቢያ ማዕከል የቱትሲዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ብቻ ነው የታሰበው ። በሁቱ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋም ማሰብ ይገባል ። እውነተኛ እርቅን ለማውረድ ከሁሉም በኩል ያለው መጥፎ ሁኔታ ግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል ። »

ኢንጋቢሬ FDRL ን በገንዘብ በመርዳት በቀረበባቸው ክስ የመሰከሩባቸው ሁለት የቀድሞው የቡድኑ አዛዦች ናቸው ። ሁለቱ አዛዦች ራሳቸው ተከሳሾች ናቸው ። የኢንጋቢሬ ጠበቃ 2 ቱ ሰዎች ጥፋተኝነታቸውን እንዳመኑ ተናግረው የመሰከሩትም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ነው ብለዋል ። ባለፈው ሚያዚያ ጉዳይቸው በፍርድ ቤት በሚታይበት ወቅት ዳኞቹ አድሎ ይፈፅማሉ ስለኔም የምስክር ቃል ለመስጠት የተዘጋጀ ሰው ቃሉን እንዳይሰጥ ከልከለዋል ሲሉ ኢንጊጊባራ ችሎቱን አቋርጠው ወጥተው ነበር ። ብሪታኒያዊው ጠበቃቸው ኢያን ኤድዋርድስ ሁኔታውን ያብራራሉ

« በመርህ ደረጃ የያዙት አቋም ከአሁን በኋላ በችሎቱ ላይ መገኘት ለችሎቱ ክብር መስጠት ይሆናል ። በርካታ ችግሮች ቢኖሩም በሁሉም ችሎቶች ላይ በመገኘት ተባብረዋል ። ነገር ግን ይሄ የመጨረሻው በፍፁም ሊዋጥላቸው ያልቻለ ነገር ነው ። »

ተንታኞች እንደሚሉት የኢንጊባሬ ግጉዳይ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ይዟል ። በነርሱ አስተያየት ክሶቹ በሩዋንዳ መንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም በ FDRL ና በ FDU Inkingi መካከል ከሚካሄደው ፖለቲካዊ ግጭት ጋር የተያያዘ ነው ። ዶክተር አሌክሳንደር ስትሮው በምሃፃሩ ጊጋ በሚባለው የአለም ዓቀፍ የአካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናት ተቋም ባልደረባ ናቸው ። በርሳቸው አስተያየት ወሳኙ ጥያቄ ከኢንጊባሬ ክስ በስተጀርባ ያለው አላማ ምንድነው የሚለው ነው ።

Rwandan opposition leader Victoire Ingabire wears handcuffs, as she listens to the judge during the her trial in Kigali, Rwanda Monday, Sept. 5, 2011. Ingabire, an outspoken critic of President Paul Kagamea's regime, is charged with allegations of providing financial support to a terrorist group, causing state security and formenting ethnic divisions. (Foto:Shant Fabricatorian/AP/dapd)

« ተወደደም ተጠላም በሩዋንዳ ህግ ከ ዘር ማጥፋት አስተሳሰቦችና ቅስቀሳዎች እንዲሁም ልዩነቶችን ከማስፋፋት ጋር የተያያዙ ንግግሮች ሊያስቀጡ ይችላሉ ። ህጎቹን መተቸት ይቻላል ፤ ሆኖም ህጎቹ አሁንም ሩዋንዳ ውስጥ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እስተያየት እንዳይሰጥ የሚከለክሉ ናቸው ። ከተፈረደባቸው ፣ ዋናው ጥያቄ የክሱ አላማ ፖለቲካዊ ነው አይደለም የሚለው ነው ። »

የኢንጊባሪ ጠበቃ ክሱ ፖለቲካዊ መሆኑ አይጠራጥርም ነው የሚሉት ። ኢንጊባሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ የሩዋንዳ መንግሥት ብቸኛዋ ተቃዋሚ አይደሉም ። በልዩ ልዩ ምክንያቶች የታሰሩ ሌሎች ተቃዋሚዎችም አሉ ። ተቃዋሚዎችን የሚያስረው የሩዋንዳ መንግሥት ደግሞ ምሥራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ አማፅያንን ይደግፋሉ ተብሎ በአንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘገባ ተጋልጧል ። በዶክተር ስትሮህ እምነት ነገ በኢንጊቤሪ ላይ ከሚሰጠው ብይን ይልቅ የተባበሩት መንግሥታት በዚህ ዘገባ ላይ የሚያሳልፈው ውሳኔ በሩዋንዳ ላይ ይበልጥ ተፅእኖ ይኖረዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 06.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/164d2
 • ቀን 06.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/164d2