የኢንተርኔት ጠለፋ እና አፈና  በግብጽ | አፍሪቃ | DW | 17.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኢንተርኔት ጠለፋ እና አፈና  በግብጽ

ማናቸውም በፌስቡክ በትዊተር እna በኢንስታግራም ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ሰው በሚዲያ ስራ እንደተሰማራ ስለሚቆጠር ቁጥጥር ስር ይወድቃል። እገዳዎቹን VPN ተብሎ የሚጠራውን በመሳሰሉ ፕሮግራሞች ለማስቀረት የሚሞክር ቢያንስ ሁለት ዓመት የሚደርስ እሥራት እና እስከ 15 ሺህ ዩሮ የሚጠጋ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:57

ግብጽ በኢንተርኔት ላይ የምታካሂደውን ቁጥጥር አጥብቃለች

​ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግብጽ ውስጥ የመብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ፣ የኢሜል መረጃ እና ልውውጣቸውን በሌላ አካል ለመከታተል  እና ለመጥለፍ የሚያስችሉ ኢሜሎች በገፍ እንዲደርሱዋቸው እየተደረገ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።  ይህ የመረጃ መጥለፊያ ዘዴ የሲብሉን ማህበረሰብ ተወካዮች ኮምፒዩተሮችንም በከፍተኛ ሁኔታ እያጠቃ ነው። ሀገሪቱ በቅርቡ የደነገገቻቸው አዳዲስ አፋኝ ህጎች እና የምትወስዳቸው እርምጃዎች በግብጽ የሚዲያ ነጻነትን፣የኢንተርኔት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችንም በእጅጉ ገድቧል። 
በኮምፕዩተርዎ ላይ ከጉግል ወይም ከማይክሮሶፍት መለያ አጠገብ  ከቀይ ማስጠንቀቂያ ምልክት ጋር «ፓስወርድዎን ወይም የሚስጥር መግቢያዎን የመስረቅ ሙከራ ተደርጓል።» የሚል ድንገተኛ ማሳሰቢያ ብቅ ይላል። ከዚያ በኋላ የማሳሰቢያ መልዕክቱ ተቀባዮች ለአካውንታቸው ለኢሜላቸው የተሻለ ጥበቃ እንዲደረግለት ይፈልጉ እንደሆነ ጥያቄ ይቀርብላቸውል፣እሺ ወይም እምቢ ከሚል ምርጫ ጋር። እሺ የሚለውን የሚጫን የኢሜል አድራሻው ይጠለፋል። ይላል ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኤሜል ጠለፋን የተመለከተ መረጃውን ያሰባሰበው ራሚ ራውፍ።
«ጠላፊው አንዴ መግቢያ ካገኘ  የኢሜል መልዕክቱን በሙሉ ለማየት እና ለመገልበጥ ከ4 ወይም ከ5 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ በቂ ነው።ከዚያ በኋላ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።ኢሜሉን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ያውሉታል።
ራሚ ራውፍ በግብጽ የዲጂታል ነጻነት የኢንተርኔት ስለላ እና ቅድመ ምርመራ ጉዳዮች አጥኚ ነው። በአሁኑ ጊዜ በርሊን የሚገኘው ራውፍ እንደሚለው ኢሜል ጠላፊዎቹ አንዳችም የቴክኒክ ክፍተት እንዲኖር አያደርጉም። ባለፉት ሳምንታት የሀሰት ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋዜጠኞች እና  አክቲቪስቶች የኢሜል መልዕክቱን ወደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስተላልፈዋል።ራውፍ እንደታዘበው በተለይ እነዚህ መልዕክቶች በብዛት ሲላኩ የነበረው የ2011 ዱ የግብጽ አብዮት በሚታሰብበት በጎርጎሮሳዊው ጥር 25 ነበር።

እነዚህ ጥቃቶች በፖለቲካዊ ምክንያቶች እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ መሆኑን ይናገራል።
 «ባለፉት 5 ዓመታት መንግሥት የሚያወጣቸው ደንቦች ዓላማ በህዝባዊ እንቅስቃሴዎችም ሆነ በግል ህይወት ውስጥ ቁጥጥሩን ማጠናከር ነው።ሰዎች ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ እና አንዳቸው ሌላኛቸውን እንዲዲሰልሉ ማድረግ።
ግብጽ በደነገጋቻቸው ህጎች አማካይነት ካለፈው ዓመት ወዲህ በኢንተርኔት ላይ የምታካሂደውን ቁጥጥር አስፋፍታለች። ከቅርብ ቀናት ወዲህ የመገናኛ ብዙሀን ደንብ አውጭዎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ደንቦች ይበልጥ አጥብቀዋል። ማናቸውም በፌስቡክ በትዊተር እንዲሁም  በኢንስታግራም ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ሰው በሚዲያ ስራ እንደተሰማራ ስለሚቆጠር በባለሥልጣናት ቁጥጥር ስር ይወድቃል።  የሚያወጧቸው መረጃዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊታገዱ እና ሊከለክሉ ቅጣትም ሊጣልባቸው ይችላሉ። እገዳዎቹን VPN ተብሎ የሚጠራውን በመሳሰሉ ፕሮግራሞች ለማስቀረት የሚሞክር ቢያንስ ሁለት ዓመት የሚደርስ እሥራት እና እስከ 15 ሺህ ዩሮ የሚጠጋ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል።ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ህጎቹ የሚያስፈልጉት በብሔራዊ ፀጥታ ስጋት ምክንያት ነው ይላሉ።በተለይ መሰረተ ቢስ እና የሀሰት ወሪዎች በፍጥነት በኢንተርኔት ስለሚሰራጩ እና አለመረጋጋትን ስለሚያስከትሉ ህጉን መደንገግ አሰፈላጊ መሆኑን በአንድ ወታደራዊ አካዳሚ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል። እርሳቸው እንደሚሉት የሀሰት ወሪዎቹ ዓላማ ህዝቡን ማሸበር እና  ተስፋ ማስቆረጥ ነው።በአሁኑ ጊዜ የግብጽ ፓርላማ አባላት የሀሰት ዜናዎችን ለመቆጣጠር ያስችላል የሚሉትን ህግ እያረቀቁ ነው። የሀሰት ዜናዎቹ ፀሀፊ የሚሉትም የታገደውን የሚስሊም ወንድማማቾች ማህበር ነው።አሁን በሀገሪቱ የሚሰራበት ህጎች አጠራጣሪ ተደርገው የሚወሰዱ መረጃዎች እንዲታገዱ ይፈቅዳሉ። በአሁኑ ጊዜ ግብጽ ውስጥ 500 የሚሆኑ ድረ ገጾች ታግደዋል። ከመካከላቸው የድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን እንዲሁም የቅርብ ጊዜው ማዳ ማርስ የተባለው ተች ድረገጾች ይገኙበታል።
በራውፍ አመለካከት በግብጽ የሚካሄደው የኢንተርኔት ቅድመ ምርመራ በሶርያ ወይም በቱርክ ከሚካሄደው ጋር ይመሳሰላል።ሲብሉን ማህበረሰብ ጸጥ እንዲል ጠንካራ ጫና አለ። ይሁን እና በርሱ እምነት ይህ አይሳካም።

Zensur im Internet

«ኢንተርኔቱን በገደብከው ቁጥር ሰዉ የተጣለበትን እገዳ አልፎ ለመሄድ ይሞክራል።በሌላ በኩል ደግሞ እርምጃው ሰዉን በማስፈራራት ሃሳቡን በኢንተርኔት ከማስፈሩ በፊት ሁለቴ እንዲያስብ ያደርገዋል።ሆኖም እኔ ተስፋ ቆርጠው ይተዉታል ብዬ አላስብም አይሆንምም።»
ራውፍ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ክፍል መታየት የለበትም ባይ ነው።ይልቁንም የህብረተሰቡ አንድ አካል ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል ይላል ።በርሱ አስተያየትነጻ ፕሬስ፣ነጻ ትምህርት ቤቶች ነጻ ራድዮ ሲኖር ኢንተርኔትም ነጻ ይሆናል።የኢንተርኔት ጠለፋ እና አፈና በግብጽ 
​ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግብጽ ውስጥ የመብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ፣ የኢሜል መረጃዎቻቸውን እና ልውውጣቸውን በሌላ አካል ለመከታተል  እና ለመጥለፍ የሚያስችሉ ኢሜሎች በገፍ እንዲደርሱዋቸው እየተደረገ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።  ይህ የመረጃ መጥለፊያ ዘዴ የሲብሉን ማህበረሰብ ተወካዮች ኮምፒዩተሮችንም በከፍተኛ ሁኔታ እያጠቃ ነው። ሀገሪቱ በቅርቡ የደነገገቻቸው አዳዲስ አፋኝ ህጎች እና የምትወስዳቸው እርምጃዎች በግብጽ የሚዲያ ነጻነትን፣የኢንተርኔት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችንም በእጅጉ ገድቧል።የዛቢነ ሮሲን ዘገባ ኂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች።
በኮምፕዩተርዎ ላይ ከጉግል ወይም ከማይክሮሶፍት መለያ አጠገብ  ከቀይ ማስጠንቀቂያ ምልክት ጋር «ፓስወርድዎን ወይም የሚስጥር መግቢያዎን የመስረቅ ሙከራ ተደርጓል።» የሚል ድንገተኛ ማሳሰቢያ ብቅ ይላል። ከዚያ በኋላ የማሳሰቢያ መልዕክቱ ተቀባዮች ለአካውንታቸው ለኢሜላቸው የተሻለ ጥበቃ እንዲደረግለት ይፈልጉ እንደሆነ ጥያቄ ይቀርብላቸውል፣እሺ ወይም እምቢ ከሚል ምርጫ ጋር። እሺ የሚለውን የሚጫን የኢሜል አድራሻው ይጠለፋል። ይላል ለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኤሜል ጠለፋን የተመለከተ መረጃውን ያሰባሰበው ራሚ ራውፍ።
«ጠላፊው አንዴ መግቢያ ካገኘ  የኢሜል መልዕክቱን በሙሉ ለማየት እና ለመገልበጥ ከ4 ወይም ከ5 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ በቂ ነው።ከዚያ በኋላ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።ኢሜሉን ሙሉ

በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ያውሉታል።
ራሚ ራውፍ በግብጽ የዲጂታል ነጻነት የኢንተርኔት ስለላ እና ቅድመ ምርመራ ጉዳዮች አጥኚ ነው። በአሁኑ ጊዜ በርሊን የሚገኘው ራውፍ እንደሚለው ኢሜል ጠላፊዎቹ አንዳችም የቴክኒክ ክፍተት እንዲኖር አያደርጉም። ባለፉት ሳምንታት የሀሰት ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋዜጠኞች እና  አክቲቪስቶች የኢሜል መልዕክቱን ወደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስተላልፈዋል።ራውፍ እንደታዘበው በተለይ እነዚህ መልዕክቶች በብዛት ሲላኩ የነበረው የ2011 ዱ የግብጽ አብዮት በሚታሰብበት በጎርጎሮሳዊው ጥር 25 ነበር። እነዚህ ጥቃቶች በፖለቲካዊ ምክንያቶች እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ መሆኑን ይናገራል።
 «ባለፉት 5 ዓመታት መንግሥት የሚያወጣቸው ደንቦች ዓላማ በህዝባዊ እንቅስቃሴዎችም ሆነ በግል ህይወት ውስጥ ቁጥጥሩን ማጠናከር ነው።ሰዎች ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ እና አንዳቸው ሌላኛቸውን እንዲዲሰልሉ ማድረግ።
ግብጽ በደነገጋቻቸው ህጎች አማካይነት ካለፈው ዓመት ወዲህ በኢንተርኔት ላይ የምታካሂደውን ቁጥጥር አስፋፍታለች። ከቅርብ ቀናት ወዲህ የመገናኛ ብዙሀን ደንብ አውጭዎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ደንቦች ይበልጥ አጥብቀዋል። ማናቸውም በፌስቡክ በትዊተር እንዲሁም  በኢንስታግራም ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ሰው በሚዲያ ስራ እንደተሰማራ ስለሚቆጠር በባለሥልጣናት ቁጥጥር ስር ይወድቃል።  የሚያወጧቸው መረጃዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊታገዱ እና ሊከለክሉ ቅጣትም ሊጣልባቸው ይችላሉ። እገዳዎቹን VPN ተብሎ የሚጠራውን በመሳሰሉ ፕሮግራሞች ለማስቀረት የሚሞክር ቢያንስ ሁለት ዓመት የሚደርስ እሥራት እና እስከ 15 ሺህ ዩሮ የሚጠጋ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል።ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ህጎቹ የሚያስፈልጉት

Marokko Internet-Cafe inTanger

በብሔራዊ ፀጥታ ስጋት ምክንያት ነው ይላሉ።በተለይ መሰረተ ቢስ እና የሀሰት ወሪዎች በፍጥነት በኢንተርኔት ስለሚሰራጩ እና አለመረጋጋትን ስለሚያስከትሉ ህጉን መደንገግ አሰፈላጊ መሆኑን በአንድ ወታደራዊ አካዳሚ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል። እርሳቸው እንደሚሉት የሀሰት ወሪዎቹ ዓላማ ህዝቡን ማሸበር እና  ተስፋ ማስቆረጥ ነው።በአሁኑ ጊዜ የግብጽ ፓርላማ አባላት የሀሰት ዜናዎችን ለመቆጣጠር ያስችላል የሚሉትን ህግ እያረቀቁ ነው። የሀሰት ዜናዎቹ ፀሀፊ የሚሉትም የታገደውን የሚስሊም ወንድማማቾች ማህበር ነው።አሁን በሀገሪቱ የሚሰራበት ህጎች አጠራጣሪ ተደርገው የሚወሰዱ መረጃዎች እንዲታገዱ ይፈቅዳሉ። በአሁኑ ጊዜ ግብጽ ውስጥ 500 የሚሆኑ ድረ ገጾች ታግደዋል። ከመካከላቸው የድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን እንዲሁም የቅርብ ጊዜው ማዳ ማርስ የተባለው ተች ድረገጾች ይገኙበታል።
በራውፍ አመለካከት በግብጽ የሚካሄደው የኢንተርኔት ቅድመ ምርመራ በሶርያ ወይም በቱርክ ከሚካሄደው ጋር ይመሳሰላል።ሲብሉን ማህበረሰብ ጸጥ እንዲል ጠንካራ ጫና አለ። ይሁን እና በርሱ እምነት ይህ አይሳካም።
«ኢንተርኔቱን በገደብከው ቁጥር ሰዉ የተጣለበትን እገዳ አልፎ ለመሄድ ይሞክራል።በሌላ በኩል ደግሞ እርምጃው ሰዉን በማስፈራራት ሃሳቡን በኢንተርኔት ከማስፈሩ በፊት ሁለቴ እንዲያስብ ያደርገዋል።ሆኖም እኔ ተስፋ ቆርጠው ይተዉታል ብዬ አላስብም አይሆንምም።»
ራውፍ ኢንተርኔት እንደተዘጋ ክፍል መታየት የለበትም ባይ ነው።ይልቁንም የህብረተሰቡ አንድ አካል ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል ይላል ።በርሱ አስተያየት ነጻ ፕሬስ፣ነጻ ትምህርት ቤቶች ነጻ ራድዮ ሲኖር ኢንተርኔትም ነጻ ይሆናል።

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic