የኢንተርኔት መረጃ ና እንቅፋቱ | ዓለም | DW | 12.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢንተርኔት መረጃ ና እንቅፋቱ

ለጋዜጠኞች መብት ደህንነት የሚሟገተው ድንበር የማይገድበው ድርጅት፡ በምሕፃሩ"አርኤስኤፍ" ምዕራባውያን መንግሥታት ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን እና የኢንተርኔት ድረ ገፅ አምደኞችን ለማፈን እና ለመሰለል በሚያደርጉት ጥረት ላይ ይረዳሉ ሲል ወቀሰ።

"አርኤስኤፍ" በኢንተርኔት ላይ የሚደረገውን ሳንሱር ታስቦ የዋለበትን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት «የኢንተርኔት ጠላቶች» በሚል ርዕስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው፡ የምዕራባውያን ኩባንያዎች ሶርያን ወይም ኢራንን ለመሳሰሉ ሀገራት ለዚሁ ተግባራቸው የሚያስፈልገውን ቴክኖሎጂ ያቀርባሉ።

ለጋዜጠኞች መብት ደህንነት የሚሟገተው ድንበር የማይገድበው ድርጅት፡ የኢንተርኔት ጠላት ያላቸው
የአምስት ሀገራት፡ ማለትም፡ የባህሬን፡ ቻይና፡ ኢራን፡ ሶርያ እና የቪየትናም መንግሥታትን የዜና አቅራቢዎችን ስራ በማስተጓጎል የመረጃ ነፃነት ዝውውርን እንደሚያፍኑ እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንደሚፈፅሙ አስታውቋል።

Feinde des Internets 2010 Flash-Galerie

ቻይና ዜና አቅራቢዎችን በማሰር በዓለም ቀዳሚውን ቦታ ይዛለች። በወቅቱ ሠላሳ ጋዜጠኞች እና ስድሳ ዘጠኝ በድረ ገፅ በንቃት የሚሳተፉ ጸሀፍት በቻይና ወህኒ ቤቶች በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ። ቻይና ከዚህ በተጨማሪም ለሷ የማይመቹ የምትላቸውን መረጃዎች ሳንሱር እንደምታደርግና በኢንተርኔት የሚወጡ ዘገባዎችንም እንደምትቆጣጠር ተገልጾዋል። ልክ እንደ ቻይና፡ የኢራን መንግሥትም ከብዙ ዓመታት ወዲህ በኢንተርኔት የሚወጡ ዘገባዎችን የመቆጣጠሩንና ሳንሱር የማድረጉን ስራ ተያይዞታል።
ለጋዜጠኞች መብት ደህንነት የሚሟገተው ድንበር የማይገድበው ድርጅት፡ የኢንተርኔት ጠላት ላላቸው የባህሬን፡ ሶርያ፡ ቻይና፡ ኢራን እና ቪየትናም በድረ ገፅ የሚወጡ ዘገባዎችን ለማፈንና ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን ለመሰለል እናለማሰር የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂ ያቀርባሉ ያላቸውን የአምስት የኮምፒውተር ኩባንያዎችን ስም አውጥቶዋል።

NO FLASH Tag der Pressefreiheit

እነርሱም፡ ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የጀርመናውያኑ እና የብሪታንያውያኑ ተቋም፡ የጀርመናውያኑ ትሮቪኮር ተቋም፡ የኢጣልያውያኑ «ሀኪንግ ቲም »፡ የፈረንሣውያኑ አሜሲ፡ እንዲሁም፡ ብሉ ኮት የተባለው የዩኤስ አሜሪካ ተቋም ናቸው። የፈላጭ ቆራጭ መንግሥታትን የአፈና ተግባር ያግዛል የሚባለው የዚህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ ዝውውር አከራካሪ በመሆኑ፡ ለጋዜጠኞች መብት ደህንነት የሚሟገተው ድንበር የማይገድበው ድርጅት፡የአውሮጳ ህብረት አባል መንግሥታት እና ዩኤስ አሜሪካ በዚሁ የኢንተርኔት የመቆጣጠሪያ እና የሳንሱር ማድረጊያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖርት ላይ ባጠቃላይ ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቦዋል። እንደሚታወሰው፡ የአውሮጳ ህብረት እና ዩኤስ አሜሪካ ወደ ኢራን እና ወደ ሶርያ በንግድ በሚላከው በዚህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ ላይ ቀደም ባሉ ጊዚያት ዕገዳ አሳርፈዋል።


ሲንኮ ሾን/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic