የኢትጵያ አካባቢያዊ ምርጫና ተቃዋሚ ፓርቲዎች | ኢትዮጵያ | DW | 15.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትጵያ አካባቢያዊ ምርጫና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

ፓርቲዎቹ ከመንግሥትና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመወያየት ፓርቲዎቹ በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሥለሆነባቸዉ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ለማግለል ተገድደዋል።አቋማቸዉን ለሕዝብ ለማስረዳት በቅርቡ አዲስ አበባ ዉስጥ የአዳራሽና የአደባባይ ሕዝባዊ ሥብሰባ እንደሚጠሩም አስታዉቀዋል

Der Meskal Square im Zentrum der äthipischen Hauptstadt Addis Abeba von der großen Tribüne aus gesehen, links im Bild die kürzlich installierte Video-Wand. Aufnahme vom Januar 2007. Foto: Peter Smolka +++(c) dpa - Report+++

የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ ሠላሳ-ሰወስት የፖለቲካ ማሕበራት በመጪዉ ሚያዚያ በሚደረገዉ አካባቢያዊና የአዲስ አበባ መስተዳድር ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ።የሰላሳ-ሰወስቱ ፓርቲዎች ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ እንዳስታወቀዉ ምርጫዉ ሠላማዊ፥ ነፃና ፍትሐዊ እንዲሆን እና ከመንግሥትና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመወያየት ፓርቲዎቹ በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሥለሆነባቸዉ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ለማግለል ተገድደዋል።ፓርቲዎቹ አቋማቸዉን ለሕዝብ ለማስረዳት በቅርቡ አዲስ አበባ ዉስጥ የአዳራሽና የአደባባይ ሕዝባዊ ሥብሰባ እንደሚጠሩም አስታዉቀዋል።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጊዚያዊ ኮሚቴዉን ሊቀመንበር አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic