የኢትዮ ጂቡቲ የማማላለሻ ችግሮች | ኤኮኖሚ | DW | 20.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የኢትዮ ጂቡቲ የማማላለሻ ችግሮች

ወደብ ኣልባዋ ኢትዮጵያ ለወጪ እና ገቢ ሸቀጧ ከሞላ ጎደል የምትጠቀመው በጂቡቲ ወደብ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚሁ የተነሳ በጂቡቲ ወደቦች ከሚስተናገዱት ገቢና ወጪ ምርቶች ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውም የኢትዮጵያ ሸቀጦች እንደሆኑ ይገመታል።

default

በዚሁ ምክንያትም ይመስላል በኣሁኑ ጊዜ የጅቡቲ መንግስት ተጨማሪ ወደቦችን እያስገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን እድሜ ጠገቡን የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመር ከመጠገን ጎን ለጎን አዲስ የባቡር ሀዲድ በመዘርጋት ላይ ይገኛል። ይህም ኣሁን በጂቡቲ ወደቦች የሚታየውን የጭነት መጨናነቅ እና የትራንስፖርት ችግሮችን በተሻለ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል።

Fregatte Köln in Dschibuti

አሮጌው የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር ሀዲድ አገልግሎት መስጥት ከማይችልበት ደረጃ ከደረሰበት ጊዜ ኣንስቶ የኢትዮጵያ ጭነቶች በመኪና ሲጉዋጉዋዙ ቆይቷል። የበረሃው መንገድ ደረጃውን ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ የጭነት ኣሰጣጡም ችግር እንዳለበት በርካታ ኣሽከርካሪዎች ያማርራሉ። ይህንኑ ችግር ለማቃለል በሚል ጭነት በማህበራት ኣማካኝነት እንዲሆን መደረጉም ለበለጠ እንግልት ዳርጎናል ይላሉ በመስመሩ የተሰማሩ ኣሽከርካሪዎች።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በመልዕክት አድራሻችን ከደረሱን መልዕክቶች ኣንዱ በጂቡቲ የጭነት ማመላለስ ተግባር ላይ ከተሰማሩት ኣሽከርካሪዎች የተላኩ ነበሩ። በመልዕክቶቹ መሰረትም ከጂቢቲ ወደብ የሚነሱ ጭነቶች በማህበራት ኣማካኝነት እንዲሆን ከተደረገ ወዲህ ኣሰራሩ ግልጽነት እየጎደለው መቷል። ኣንዳንድ ማህበራት ወዲያውኑ ጭነት ሲያገኙ ሌሎች ደግሞ ለቀንት እና ኣንዳንዴም ለሳምንታት ይጉላላሉ ተብሏል። ጭነት ተገኘ ሲባልም ኣንዳንድ ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈቀዱ ኣሽከርካሪዎች እንደሚሉት ለተመረጡ ማህበራት ቀላል ያሉ ጭነቶች እየተፈቀዱ የተቀሩት ግን የመኪና ወገብ የሚቆርጥ ከባድ ጭነት እንዲያነሱ ይገዳዳሉ እየተባለ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመለከተውን ኣካል ምላሽ ለማግኘት መጀመሪያ የሞከርነው ወደ ኢትዮጵያ የባህር ትራንዚት እና ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሺን ነበር። ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለስልጣንን እንደሆነ ተነግሮን ወ,ደዚያው ደወልን ። አቶ ብስራት የተባሉ የስራ ኃላፊ ግን መታችሁ ማየት ትችላላችሁ ከማለት ያለፈ የተጨበጠ ምላሽ ለመስጠት ኣልፈለጉም። ፍርዱን ለህዝብ ትተናል ።

ጃፈር ዓሊ

ሸዋዬ ለገሠ