የኢትዮ-ጀርመን የትምሕርት ስምምነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የኢትዮ-ጀርመን የትምሕርት ስምምነት

አዲስ አበባ ዉስጥ በተፈራረሙት ዉል መሠረት ሁለቱ ሐገራት ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ አርባ ኢትዮጵያዉያን የምሕንድስና ተማሪዎችን በጋራ ያስተምራሉ።

የኢትዮጵያና የጀርመን መንግሥታት በየዓመቱ አርባ የምሕንድስና ተማሪዎችን በዶክትሬት ዲግሪ በጋራ ለማስተማር ተስማሙ።የኢትዮጵያ የትምሕርት ሚንስቴርና የጀርመኑ የአካዳሚ ልዉዉጥ ተቋም ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ዉስጥ በተፈራረሙት ዉል መሠረት ሁለቱ ሐገራት ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ አርባ ኢትዮጵያዉያን የምሕንድስና ተማሪዎችን በጋራ ያስተምራሉ።ተማሪዎቹ ትምሕርታቸዉን በሰወስት ዓመት እስኪያጠናቅቁ ድርስ በዓመት ስድስት ወር ኢትዮጵያ የተቀረዉን ሥድት ወር ደግሞ ጀርመን እየቆዩ ያጠናሉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ስምምነቱን የተፈራረሙትን ወገኖች አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ እነሆ

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic