የኢትዮ- አሜሪካ ግንኙነትና የሰብአዊ መብት ጥያቄ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 04.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮ- አሜሪካ ግንኙነትና የሰብአዊ መብት ጥያቄ፣

ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ እ ጎ አ ከ 1903 ዓ ም አንስቶ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት መሥርተው የሚገኙናበተለይ ከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የጋራ ትብብርን አጠናክረው የሚገኙ አገሮች ናቸው። በመንግሥታት ደረጃ ግንኙነቱ ያልሠመረው በደርግ

የአስተዳደር ዘመን ነው። ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ ፣ አንዱ ከሌላው የሚቀስማቸው በጎ እሴቶች ይኖራሉ። በሳይንስና ቴክኖሎጂ ከመጠቀችው አሜሪካ፣ ለሁለንተናዊ ዕድገት ያበቃ ትምህርት ፤ ምርምርና ከመሳሰለው ሌላ፤ ሰውን በነጻ መንፈስ የማሰብና የመሥራት መብት ያጎናጸፈው ከ 230 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ጽኑ ሕገ መንግሥት፤ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ሊጠቀሱ ይችሉ ይሆናል። ኢትዮጵያ ፤ ራሷን የዩናይትድ ተጓዳኝ እስካደረገች ድረስ፤ እጅግ ጠንካራ ከሆነ ወዳጅ፤ የሚቀሰሙ በዛ ያሉ ጠቃሚ ጉዳዮች አይታጡም። ይሁን እንጂ፤ ባለፉት የኢትዮጵያ ገዥዎችና በዛሬዎቹም፣ ዝንባሌው ፤ ፍላጎቱ ፤ ነበረ? አሁንስ አለ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ሊያስነዝር ይችል ይሆናል።

ከ 2 ወራት ገደማ በፊት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፤ እ ጎ አ የ 2013 ን የተለያዩ ሃገራት የሰብአዊ መብት አያያዝ ዘገባ ሲያቀርብ፤ የኢትዮጵያውንም በሰፊው ዳስሶታል። ከዚያ ወዳጅ ሀገር ከሰነዘረው ወቀሳ ኢትዮጵያ የቀሰመችው ትምህርት አለ?

የኢትዮ- አሜሪካ ግንኙነትና የሰብአዊ መብት ጥያቄ፣ ዛሬም የውይይታችን ርእስ ነው። ለውይይቱ እንግዶችን ጋብዘን ፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እንደሚሳተፉ ቃል የገቡልንን እንግዳ ፤ ውይይቱ ሐሙስ ከቀትር በኋላ ከሚቀረጽበት ጊዜ ጀምሮ እስከፍጻሜው በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የገዥውን ፓርቲ አቋም ከሚደግፉ ጦማሪዎች መካከል አንድ ለማሳተፍ ያደረግነው ሙከራም አልሠመረም። ውይይቱን ከ ተገኙልን 3 እንግዶችን ጋር አካሂደናል። እነርሱም። የህግ ባለሙያና ጦማሪት ሶሊያና ሽመልስ፤ ቀድሞ የሰብአዊ መብቶች ጉባዔ የምርመራ ሠራተኛና አሁን በብራሰልስ፤ ቤልጂም የሰብአዊ መብት አጥኚ አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም፣ እንዲሁም ጋዜጠኛና በዋሽንግተን ዲሲ የዶቸ ቨለ ዘጋቢ፤ አበበ ፈለቀ ናቸው። ውይይቱን እንዲያዳምጡ እንጋብዛለን።

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic