የኢትዮ-ቴሌኮም አስተዳደር | ኢትዮጵያ | DW | 02.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮ-ቴሌኮም አስተዳደር

ኢትዮ ቴሌኮም ለሁለት ዓመታት ለፍራንስ ቴሌኮም ሰጥቶ የቆየዉን የአስተዳደር ሥራ ኃላፊነት የሥራ ዉል በሀገር ዉስጥ ባለሙያዎች መቀየሩን ዛሬ አስታወቀ።

መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የስራ ዉል ተሰጥቶት የቆየዉ የዉጭ ድርጅት በስልጠና፤ ስልቱን ዘመናዊ በማድግና አግልግሎት በማዳረስ ረገድ የሚጠበቅበትን በማከናወኑ ሊሸለም እንደሚገባዉ ማመልከቱን በስፍራዉ የተገኘዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ገልፆልናል። የቴኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ዛሬም የሚያነሷቸዉ ችግሮች መኖራቸዉን ድርጅቱ በማመንም ይሻሻላሉ የሚል ተስፋ ሰጥቷል። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ ስለጋዜጣዊ መግለጫዉ ፍሬ ሃሳብና የተነሱ ጉዳዮችን እንዲገልፅልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic