የኢትዮ-ቤተ እስራኤላውያን ቁጣና ተቃውሞ | ኢትዮጵያ | DW | 01.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮ-ቤተ እስራኤላውያን ቁጣና ተቃውሞ

እስራኤል ኢየሩሳሌም ዉስጥ ለፀረ ዘረኛነት ሰልፍ አደባባይ የወጡ ኢትዮጵያዉን ቤተ-እስኤላዉያን ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸዉ ተመለከተ። ትናንት ለተቃዉሞ የወጡት ቤተ-እስራኤላዉያኑ ኢትዮጵያዉያን እስራኤል ዉስጥ በቆዳ ቀለማቸዉ እንደተገለሉ የሚያመለክቱ መፈክሮችን ይዘዉ መዉጣታቸዉ ተዘግቧል።ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን እስራኤል ውስጥ የሚፈፀምባቸው ዘረኝነት እንዲቆም ጥሪያአቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። ከአንድ ሺህ በላይ የተገመቱ ቤተ እስራኤላውያን ትናንት እየሩሳሌም ውስጥ ቁጣቸውን በገለፁበት የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊሶች በዘረኝነት የሚወስዷቸው እርምጃዎች እንዲቆሙ ጠይቀዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የእስራኤል ፖሊሶች ዩኒፎርም የለበሰ ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊ ወታደር ሲደበደቡ የሚያሳይ ቪድዮ ከተለቀቀ ወዲህ የቤተ እስራኤላውያኑ ቁጣ ተባብሷል። ኢትዮ-ቤተ እሥራኤላውያኑ በትናንቱ ሰልፍ ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች ውስጥ «አውሮፓ ውስጥ አይሁዶች በአይሁድነታቸው ይገደላሉ እዚህ ደግሞ ፣አይሁዶች ጥቁር በመሆናቸው ይገደላሉ» የሚል መፈክር ይገኝበታል። ኢየሩሳሌም ከተማ በታየዉ በዚሁ የተቃዉሞ ሰልፍ ከ1000 የሚበልጡ ሰልፈኞች ተሳታፊ ነበሩ። ኢትዮጵያዉያን ቤተ-እስራኤላዉያኑ ሰልፈኞች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያሚን ኔታንያሁ ቢሮ ለማምራት ሲንቀሳቀሱ ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝና ዉኃ ሰልፉን ለመበተን ሙከራ አድርጎ ነበር። ይህ የፖሊስ ርምጃ ያስቆጣዉ ሰልፈኛ ፖሊስ ላይ ድንጋይና ጠርሙስ በመወርወር ከፖሊስ ጋር መጋጨቱ ተገልፆአል። የእየሩሳሌሙን ዘጋቢያችንን ዜናነህ መኮንን ተቃውሞው እስከ ዛሬ ተሸፋፍኖ የቆየው ዘረኝነት በአደባባይ እንዲወጣ አድርጓል ይላል።

ዜናነህ መኮንን

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic