የኢትዮ-ሶማሌ ሹማምት ሽኩቻ አበቃ ይሆን? | ኢትዮጵያ | DW | 03.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮ-ሶማሌ ሹማምት ሽኩቻ አበቃ ይሆን?

አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር፣ ባለፈዉ ነሐሴ ከሥልጣን በተወገዱ ማግሥት የፓርቲዉን የሊቀመንበርነት ሥልጣን በያዙት በአቶ አሕመድ ሽዴና የክልሉን የምክትል ርዕሠ-መስተዳድርነት ስልጣን በያዙት በአቶ ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር መካከል ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ ሲደረግ ነበር

የኢትዮጵያ ሶማሌ መስተዳድር ገዢ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶሕዴፓ) አባሉ ያልነበሩትን የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድርን የፓርቲዉ ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ጅጅጋ ዉስጥ ለሰወስት ቀን የመከረዉ የፓርቲዉ ጉባኤ የፓርቲዉን የእስካሁን ሊቀመንበር የገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴን በሊቀመንበርነታቸዉ እንዲቀጥሉ ወስኗል። የቀድሞዉ የሶማሌ ርዕሠ መስተዳድርና የፓርቲዉ ሊቀመንበር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር፣ ባለፈዉ ነሐሴ ከሥልጣን በተወገዱ ማግሥት የፓርቲዉን የሊቀመንበርነት ሥልጣን በያዙት በአቶ አሕመድ ሽዴና የክልሉን የምክትል ርዕሠ-መስተዳድርነት ስልጣን በያዙት በአቶ ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር መካከል ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ ሲደረግ ነበር። የፓርቲዉ ጉባኤ ሁለቱን ፖለቲከኞች የበላይና የበታች አድርጎ መሾሙ ሽኩቻዉ መቀዛቀዙን ጠቋሚ ነዉ ባዮች አሉ። ጉባኤዉ ከሁለቱ ሹመት በተጨማሪ የፓርቲዉን ሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መርጧል። አርማዉን አሻሽሏል፣የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሚለዉን ስያሜዉንም «የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ» (ሶዴፓ) ወደሚል ቀይሮታል። ጉባኤዉን የተከታተለዉ መሳይ ተክሉ እንደዘገበዉ በጉባኤዉ መዝጊያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ተገኝተዉ እንደነበር ወኪላችን መሳይ ተክሉ ከጅግጅጋ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ