የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብና አንድምታው | ኢትዮጵያ | DW | 29.11.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብና አንድምታው

ሱዳን የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮቿን እንደገደሉ ገልጻለች ተብሎ መነገሩን የኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ አደረገ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን እንዳሳወቀው ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብ አሁንም በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አማራጮችን በመመልከት ላይ ትገኛለች፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:25

ሰርጎገብ በተባሉ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዶአል

 

ሱዳን የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮቿን እንደገደሉ ገልጻለች ተብሎ መነገሩን የኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን እንዳሳወቀው ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብ አሁንም በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አማራጮችን በመመልከት ላይ ትገኛለች፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ የከፈተችው ተኩስ አለመኖሩን የገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን በኩል የሚመጡበትን ሰርጎገብ ያሏቸው አካላትን ለመመከት ግን ግን እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

በጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ በበኩላቸው ሂደቱ በውስጥ ቀውስ ላይ የተጠመደው የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና የማብዛት ሙከራያ ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

ስዩም ጌቱ  

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic