የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ | ኢትዮጵያ | DW | 16.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ

በታህሳስ ወር 2008 ድንበር ማካከል እንደሚጀመር አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዉ ነበር። ይህን ተከትሎም የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተሟጋቾች የኢትዮጵያ መንግሥት > ነዉ ሲሉ ተችተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:26
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:26 ደቂቃ

ድንበር ክለላ

ይሁን እንጂ በዛዉ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምንም <<ምስጢራዊ የድንበር ክለላ>> እንደሌለ እና ሁለቱም ሃገራት በድንበሮች አካባቢ <<ሰላምና መረጋጋት>> ላይ አብረዉ እየሠሩ መሆናቸዉን ተናገሩ። አሁንም ቢሆን ግን የድንበር ክለላዉ በኅብረተሰቡ ዘንድ ዋነኛ የመወያያ ርእስ ሆኖ ቀጥሏል።
ይህ የድንበር ክለላ ግዜዉ በርግጥ መቼ እንደሚሆን ባይታወቅም ወደ 750 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፊን እና በዚህ አካባብ የሚኖሩም በሽህ የሚቆጠሩ ገበሬዎች እንዳሉ ዘገባዎች ያሳያሉ። የአርማጭሆ አካባቢ ተወላጅ የሆነዉ ዳንኤል ጥላሁን ለዶቼ ቬለ የድንበር ክላዉን በተመለከተ ከማኅበራዊ ደረገፆች እና አንዳንድ የዉጭ መገናኛ ብዙሃን ካልሆነ ከአገር ዉስጥ ምንም መረጃ እንደሌለዉ ገልጿል።


ዳንኤል ጥለሁን የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ሲሆን አብሮት የሚማሩ ተማርዎችን ጨምሮ አብዛኛዉ ኅብረተሰብ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ሊካለሉ ቀርቶ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር እንዳላቸዉ እንኳ የማያዉቁ አሉ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። በእርግጠኝነት የት ቦታ እንደሚካከል ዳንኤል ባያዉቅም ሊሆን ይችላል የሚለዉ ወይ ከመተማ፣ ወይ ከቋራ ወይም ሰፊ የእርሻ መሬት ያለበት ዴሌሎን ሊያጠቃልል እንደሚችል ይናገራል። ይህ የእርሻ መሬት ሱዳኖች የኛ ነዉ እያሉ በአካባቢዉ ማሳ ላይ ጥቃት እንደሚያደርሱም ዳንኤል ሳይገልፅ አላለፈም።

Karte Äthiopien englisch


ለደኅንነታቸዉ ሲባል ስማቸዉ እንዳይጠስ የጠየቁት የመተማ አካባቢ የገንዳዋ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑት ሌላኛዉ አስተያየት ሰጪ በዴሌሎ ከፍተኛ የድንበር ግጭት እንደሚታይ እና ሱዳኖች ወደ ዉስጥ ገብተዉ እንደሚያርሱም ይናገራሉ።
በመንግሥት ደረጃ ድንበር ክለላዉን በተመለከተ ለኅብረተሰቡ ይህ ነዉ የተባል ነገር ባይኖርም ይላሉ እኝህ የመተማ አካባቢ ነዋሪ፤ አንዳንድ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች <<አፈትልከዉ>> የሚወጡ መረጃዎች ድንበር ክለላዉ ሊካሄድ እንደሚችል ይጠቁማሉ።


ጉዳዩን አስመልክቶ በዶቼ ቬሌ ደረ-ገፅ ላይ በተደረገዉ ዉይይት አስተያየት ሰጭዎቹ መንግስት ክለላዉን ሳይጀምር ከኅብረተሰቡ ጋር መወያየት እንዳለበት ጠቁመዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች